“አሰባሳቢ ገዢ ትርክት ለሀገረ መንግስት ግንባታ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

“አሰባሳቢ ገዢ ትርክት ለሀገረ መንግስት ግንባታ” ፡ 3ኛው ከተማ አቀፍ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ።

“አሰባሳቢ ገዢ ትርክት ለሀገረ መንግስት ግንባታ” ፡ 3ኛው ከተማ አቀፍ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ።

ጥር 03 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

አሰባሳቢ ገዢ ትርክት ለሀገረ መንግስት ግንባታ በሚል መሪ ቃል 3ኛው ከተማ አቀፍ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሀ ግብር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አመራሮችና ነዋሪዎች በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል ።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን በየክፍለ ከተማው የሚካሄዱ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራሞች እንደ ሀገር የሚያስተሳስሩንን የጋራ እሴቶች የምናጠናክርበት ነው፤” በማለት የአሰባሳቢ ትርክት አስፈላጊነትን ገልጸዋል።

“ጠንካራ ሀገረ መንግስት የሚገነባው በጤናው የተጠበቀና በስራ ስነ-ምግባር የታነጸ ዜጋ ሲኖር ነው ያሉት አቶ በላይ ስፖርት ደግሞ ለዚህ ዓይነተኛ መሳርያ ነው ብለዋል

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ም/ስራ ዋና አስኪያጅ ወ/ሮ ውቢት ዮሐንስ በበኩላቸው የብዙሃን ስፖርት መርሀ ግብሮች በህብረተሰቡ ዘንድ የእርስ በእርስ ግንኙነትን በመፍጠር አንድነትን፣ ፣ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን የሚጠናከር በመሆኑ በክፍለ ከተማው ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

https://linktr.ee/YouthandSport1

#የሀገረመንግስትግንባታ #አሰባሳቢትርክት #የብዙሃንስፖርት #ጤናማዜጋ

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.