የነገዎችን ኮከቦች ፍለጋ: የ10 ዓመቱ ጉዞ ከታዳጊዎች ምልመላ ይጀምራል።
የነገዎችን ኮከቦች ፍለጋ: የ10 ዓመቱ ጉዞ ከታዳጊዎች ምልመላ ይጀምራል።
አቶ በላይ ደጀን በየክፍለ ከተማው እየተከናወነ የሚገኝውን የተተኪ ብሔራዊ ቡድን ምልመላ ሂደት በአካል ተገኝተው ተመልክተዋል።
ጥር 03 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን በየክፍለ ከተማው እየተከናወነ የሚገኝውን የተተኪ ብሔራዊ ቡድን ምልመላ ሂደት በአካል ተገኝተው ምልከታ አካሂደዋል።
ለሀገር ኩራት የሚሆን ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት መሰረቱ ታዳጊዎች ላይ መስራት መሆኑን የጠቁሙት አቶ በላይ ደጀን ምልመላው ፍፁም ግልፅነት ባለውና ተስጥኦን ብቻ መሰረት ባደረገ መልኩ እንዲካሄድ አሳስበዋል።
የቢሮ ሀላፊው በአራዳ ክፍለ ከተማ ቤለር ሜዳ እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው የታዳጊዎች ማሰልጠና ፕሮጀክት ተገኝተው ምልከታ በማድረግ ታዳጊዎችን አበረታተዋል።
የምልመላው አለማ የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በቀጣይ 10 ዓመታት ውስጥ ''አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን'' ለመገንባት ያስቀመጡትን ታላቅ ሀገራዊ ኢኒሼቲቭ ስኬታማ ለማድረግ ያለመ ነው።
https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.