የወርቃማ ሰኞ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ። ጥር 04 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የወርቃማ ሰኞ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ።
ጥር 04 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ዘወትር ሰኞ ከስራ ስዓት መግቢያ በፊት የሚያካሂደውን የወርቃማ ሰኞ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር አካሂዷል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች፣ ጠቅላላ ካውንስል አባላት፣ የፌዴሬሽን ፅ/ቤት ሀላፊዎች እና ሰራተኞች ተገኝተዋል።
ስራን በሐላፊነት ስሜት መስራት እንደሚያስፈልግ የሚያስረዳ ኒፖቲዝም በሚል ርዕሰ ጉዳይ የተዘጋጀ ሰነድ በአቶ ይድናቃቸው ሀይሉ የቢሮው የወጣት አደረጃጀት የክትትልና ድጋፍ ባለሙያ አቅርበዋል።
ሁሉም ሰራተኛ ስራውን በሀላፊነት እና በተጠያቂነት ስሜት መስራት እንደሚገባ እንዲሁም የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት ከቢሮው ሀላፊ እስከ ባለሙያው የተናበበ ስራን መስራት እንደሚያስፈልግ በሰነዱ ተመላክቷል።
በእውቀት ሽግግር መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራን በእውቀት ሽግግር መርሀ ግብሩ ላይ የሚቀርቡ ጉዳዮችን ወደ ተቋማዊ አሰራር በመቀነር ተግባራትን በተሻለ አፈፃፀም ለመተግበር እንደሚረዳ ተናግረዋል።
https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.