መንግስት ለዘርፉ በሠጠው ልዩ ትኩረት ስኬታማ ስ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

መንግስት ለዘርፉ በሠጠው ልዩ ትኩረት ስኬታማ ስራዎችን መስራት ተችሏል፤ (ክብርት ሸዊት ሻንካ)

መንግስት ለዘርፉ በሠጠው ልዩ ትኩረት ስኬታማ ስራዎችን መስራት ተችሏል፤

(ክብርት ሸዊት ሻንካ)

ጥር 04 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

ክብርት ሸዊት ሻንካ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር መንግስት ለባህል ጥበባትና ስፖርት ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት ባለፉት 6 ወራት ስኬታማ ስራዎችን መስራት ተችሏል ብለዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር "የባህል፣ ጥበባትና ስፖርት ዕምርታ ለኢትዮጵያ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሴክተር ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል።

ከብርት ሸዊት በጉባኤው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በባህል ጥበባትና ስፖርት ዘርፍ ባለፉት 6 ወራት የላቀ ስኬት መከናወኑን ገልፀዋል።

ለዘርፉ ስኬትም ከላይ እስከ ታች ያለው አመራር፣ ባለሙያ፣ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ህዝብን በማስተባበር የተከናወኑ ስራዎች መሆኑን አስገንዝበዋል።

መንግስት ለስፖርት ልማት በሰጠው ልዩ ትኩረት ውድድሮችን በማስቀጠል፤ ነባሩን የስፖርት ፖሊሲ በማሻሻል ማፀደቅ፤ በዓለምአቀፍ መድረክ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደተቻለ በንግግራቸው አንስተዋል።

አጠቃላይ በሀገራችን ጥርጊያ ሜዳዎችን ጨምሮ 43,335 የይዞታ ማረጋገጫ ያላቸው ስፍራዎች ያሉ ሲሆን 15,796 ሜዳዎች ባለፉት 8 ዓመታት ብቻ

የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ያገኙ መሆናቸውን ክብርት ሸዊት ገልፀዋል።

የስፖርት ልማት ስኬትን ለማረጋገጥ በታዳጊ ልማት ስራዎች ላይ መንግስት በላቀ ደረጃ መስራቱን ያነሱት ሚኒስትሯ ከትላልቅ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ አንፃር የተጀመሩ ስራዎች ግንባታቸው እየተፋጠነ ይገኛል ብለዋል።

ከጥበባት ዘርፍ አንፃር የኢትዮጵያን መልክ አጉልተው የሚያሳዩ የጥበብ ስራዎች የተሰሩበት፤ ታላላቅ ኮንፈረንሶና መድረኮች የተካሄዱበት መሆኑም ተገልጿል።

የህዝብ እና የአደባባይ በዓላትን በመጠቀም የህዝብ ለህዝብ ትስስር የተፈጠረበት፤ የቋንቋና የበዓላት ፕሮፋይል የተሰነደበት፣ የጥናትና ምርምር ስራዎች ከባህልና ቋንቋ ዘርፍ አንፃር መከናወናቸውን ክብርት ሸዊት በንግግራቸው አካተዋል።

ጉባዔው ባለፉት 6 ወራት የተሰሩ መልካም አጋጣሚዎችን በማላቅ እንዲሁም በጉድለት የተለዩ ጉዳዮችን በመለየት ለቀጣይ ለበለጠ አፈፃፀም ለመዘጋጀት ዓላማ ያደረገ እንደሆነም ሚኒስትሯ አስገንዝበዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እያካሄደ ባለው የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የሴክተር ጉባኤ አቶ እንድሪስ አብዱ የስትራቴጅክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ የ6 ወራት የሴክሩን አፈፃፀም አቅርበዋል።

አንባቢ ትውልድን ከመጠር አንፃር 436 ቤተ መፃህፍት አገልግሎት ላይ የሆኑ 9 የሚሆኑት በመደመር ትውልድ መፅሐፍ ሽያጭ የተገነቡ መሆናቸው። 39 ሲኒማ ቤቶች፣120 ፕላዛዎች እና 53 አንፊ ቴአትር ስፍራዎች ለጥበባት ወርፉ ክፍት መሆናቸው። የትርጉም እና አስተርጓሚነት ማህበር መቋቋም፤ የብሔራዊ ስፖርት ፕሬዚዳንቶች በአህጉር እና ዓለምአቀፍ ማህበራት ውስጥ በአመራርነት ሚና ተፅዕኖ እየፈጠሩ መሆኑ፤ ከህዝባዊ አካላት ጋር በትብብር በመስራት ውጤት መምጣቱ ፣ የየዘርፉ ዲፕሎማሲ፣ የስፖርት ማህበራት ወደ ሪፎርም መግባት የተጠቀሱ ጉዳዮች ናቸው።

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.