በባዶ እግሩ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጉብኝት የጀ...

image description
- ውስጥ supporter    0

በባዶ እግሩ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጉብኝት የጀመረው አይሾው ስፒድ በአዲስ አበባ የተሰሩ የልማት ስራዎችንም እየጎበኘ ይገኛል ጥር 5 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

በባዶ እግሩ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጉብኝት የጀመረው አይሾው ስፒድ በአዲስ አበባ የተሰሩ የልማት ስራዎችንም እየጎበኘ ይገኛል

ጥር 5 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

ታዋቂ አሜሪካዊው ዩቲዩበር እና የቀጥታ ስርጭት አቅራቢ ዳረን ዋትኪንስ ጁኒየር በቅጽል ስሙ አይሾው ስፒድ የተሰኘው ቲክቶከር እና ዩቱዩበር በባዶ እግሩ በዓድዋ ድል መታሰቢያን የጀመረው ጉብኝት በአዲስ አበባ የተሰሩ የልማት ስራዎችን እየጎበኘ ነው፡፡

የ21 ዓመቱ አሜሪካዊ ዳረን ጄሰን ዋትኪንስ ጁኒየር በአሁኑ ወቅት "Speed Does Africa" የተሰኘ ጉዞ እያደረገ ሲሆን÷ አዲስ አበባ ሲደርስ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ አቀባበል እንዳደረጉለት ተመልክክቷል፡፡

አይሾው ስፒድ በቲክቶክ ላይ በሚለቃቸዉ የራሱ አጫጭር ቪዲዮዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በአጭር ጊዜ ዉስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮችን አግኝቷል።

በ20 የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እያደረገ የአፍሪካን ባህልና ታሪክ ለዓለም እያስተዋወቀ የሚገኘው ታዋቂ ዩቲዩበሩ÷ በኬንያ በነበረው ቆይታ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ከ300 ሺህ በላይ አዲስ ተከታዮችን በማግኘት የዩቲዩብ ተከታዮቹን ቁጥር 48 ሚሊየን ማድረሱ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.