አይ ሾው ስፒድ" ገና ተጫወተ፤ ጥር 05 ቀን 2...

image description
- ውስጥ supporter    0

አይ ሾው ስፒድ" ገና ተጫወተ፤ ጥር 05 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢ

አይ ሾው ስፒድ" ገና ተጫወተ፤ ጥር 05 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በዓለማችን ላይ ከሚገኙ ግንባር ቀደም ተፅዕኖ ፈጣሪ የማህበራዊ ሚዲያ ከዋክብት መካከል ስሙ በዋናነት የሚጠቀሰው "አይ ሾው ስፒድ" ዛሬ ኢትዮጵያ መግባቱ የሚታወቅ ሲሆን ተወዳጁ ባህላዊ ጨዋታ የሆነውን ገናን ተጫውቷል። በኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት ቤተ-መንግስት ውስጥ በሚገኝ ሜዳ በተካሄደው ጨዋታ አይ ሾው ስፒድ ከስፖርት ጋዜጠኞች፣ ታዋቂ የገና ተጫዋቾች እና ቲክተሮች ጋር ተጫውቷል። በ "Streamy Awards" ላይ የዓመቱ ምርጥ "Breakout Streamer" ሽልማትን ማሸነፍ የቻለው አይ ሾው ስፒድ በአንድ ወቅት "Siuuu!" የሚለውን የክርስቲያኖ ሮናልዶ ደስታ አገላለጽ በመጠቀም እርሱን ለማግኘት ባደረጋቸው በርካታ አዝናኝ ጥረቶች ቡዙዎቹ ያውቁታል። ታዋቂው ዩቲዩበር አይ ሾው ስፒድ በአሁኑ ወቅት "Speed Does Africa" በተሰኘ መርህ የአፍሪካ ሀገራትን በሰፋት እየጎበኘ የሚገኝ ሲሆን በ28 ቀናት ውስጥ 20 የአፍሪካ ሀገራትን ለመጎብኘት አቅዶ በመነሳቱ በሄደባቸው ሀገራት ሁሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ትኩረት እየሳበ ይገኛል።

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.