ሲቪክ ማህበራት በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከፍተኛ አስተወጽኦ እየተወጡ እንደሚገኝ ተገለጸ ጥር 6 ቀን 2018 ዓ. ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
ሲቪክ ማህበራት በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከፍተኛ አስተወጽኦ እየተወጡ እንደሚገኝ ተገለጸ ጥር 6 ቀን 2018 ዓ. ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከሲቪክ ማህራት ጋር የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት ማህበራቱ በበጎ ፍቃድ አገልግሎት እና በሰላምና ጸጥታ ስራዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ እየተወጡ እንደሚገኝ ተገለጸ በ2018 በጀት የመጀመሪያው መንፈቀ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በተገመገመበት ወቅት የአዲስ አበባ ወጣት ማህበር፣ ብሄራዊ ደም ለጋሾች ማህበር አዲስ አባ ቅርጫፍ እና የአዲስ አበባ ትራክ በጎ ፍቃድ ማህበር አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ ሲቪክ ማህበራት ከቢሮው ጋር በመቀናጀት እየሰሩ ያለው ጠንካራ ስራ በሀገረ መንግስት ግንባታ እና ከወጣቶች ተጠቃሚነት ላይ የጎላ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኝ የገለጹት የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብርዓለም ደምሴ ማህበራቱ በቀጣይ በሚደረጉ የስራ ዕድል ፈጠራና የበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የሲቪክ ማህበራቱ ባላፉት 6 ወራት ያከናወኑት ስራ ላይ ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በከተማችን የሰላምና ጸጥታ ተግባር እና የልማት ስራዎች ውስጥ ያላቸውን ሚና አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመልክቷል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.