የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት...

image description
- ውስጥ supporter    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት አፈጻጸምን ከሠራተኞች ጋር ገመገመ ጥር 07 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት አፈጻጸምን ከሠራተኞች ጋር ገመገመ

ጥር 07 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን በተመለከተ ከጠቅላላ ሠራተኞች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ።

በመድረኩ ላይ ያለፉት ስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ በወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ፣ በስፖርት ልማትና በማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ ረገድ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርበዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ለሠራተኞች የስራ መመሪያና መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ባለፉት ስድስት ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች የጋራ ጥረት ውጤት መሆናቸውን ጠቅሰው፤ የታዩ የአፈጻጸም ክፍተቶችን በዝርዝር በመለየት በቀሪው የበጀት ዓመት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሠራባቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተለይም የከተማዋን ወጣቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የስፖርት ሁለንተናዊ ልማትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ሠራተኛው በቁርጠኝነትና በቅንጅት መስራት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል ተናግረዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ሠራተኞችም በሪፖርቱ ላይ ያላቸውን አስተያየት የሰጡ ሲሆን፣ በቀጣይ ስድስት ወራት ዕቅዶችን በውጤታማነት ለማጠናቀቅ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ቢሮው በቀጣይ ግማሽ ዓመት የወጣቶች ማዕከላትን አገልግሎት ማዘመን እና የታላላቅ ስፖርታዊ ውድድሮችን ስኬታማነት በዋና ትኩረት እንደሚሠራ በመድረኩ ተመላክቷል።

https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.