ከተማ አስተዳደሩ ለስፖርት ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት ባለፉት 6 ወራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል! ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጥር 07 ቀን 2018ዓ.ም
ከተማ አስተዳደሩ ለስፖርት ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት ባለፉት 6 ወራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል! ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጥር 07 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለስፖርቱ ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት ባለፉት ስድስት ወራት በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢር ገልጿል ቢሮው ከከተማ እስከ ወረዳ ካሉ የዘርፉ አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር በበጀት አመቱ የ6 ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ዙሪያ የውይይትና የግምገማ መድረክ አካሂዷል። በውይይቱ ላይ የተገኙት የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የተመዘገቡት ውጤቶች የሚበረታቱ መሆኑን ገልጸው፣ በቀጣይም ስፖርቱን በከተማችን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግና የከተማዋን ስም በስፖርቱ ዓለም ከፍ ለማድረግ ከከተማ እስከ ወረዳ ያለው አመራርና ባለሙያ በቅንጅትና በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል። ቢሮው ባለፋት 6 ወራት በስፖርት ዘርፍ ካስመዘገባቸው ዋና ዋና ውጤቶች ውስጥ ደረጃቸውን የጠበቁና ለህዝብ ክፍት የሆኑ 15 የማዘውተሪያ ስፍራዎችን መገንባታቸው። ከ250 በላይ ኤሊት ስፖርተኞችን በማፍራት በክለቦች፣ በአካዳሚ እና በብሔራዊ ቡድን እንዲመረጡ ማድረጉ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ መገንባት መቻሉና በሀገር አቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮች አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ በሪፖርቱ ተመላክቷል https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.