በ6 ወራት ውስጥ ከ96 ሺህ በላይ የከተማው ወጣቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆን ችለዋል። አቶ በላይ ደጀን ጥር 07 ቀን 2018ዓ.ም
በ6 ወራት ውስጥ ከ96 ሺህ በላይ የከተማው ወጣቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆን ችለዋል። አቶ በላይ ደጀን ጥር 07 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን አስመልክቶ ከቢሮው ሰራተኞች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ ላይ የቢሮው ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን እንደገለጹት፤ ባለፉት ስድስት ወራት ለወጣቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና ለስፖርት ልማት እድገት ልዩ ትኩረት በመሰጠቱ አበረታችና ስኬታማ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል። ከ264 ሺህ በላይ ወጣቶች በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 96 ሺህ በላይ የሚሆኑት የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን አቶ በላይ ተናግረዋል ብቃት ያላቸው ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት በ20 የስፖርት አይነቶች በ710 የስልጠና ጣቢያዎች ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝ የገለፁት የቢሮ ሀላፊው ከ250 በላይ ኤሊት (Elite) ስፖርተኞችን ማፍራት እንደተቻለ ተናግረዋል ። 15 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ባለፉት 6 ወራት ተገንብተው ለህብረተሰቡ ለአገልግሎት እንዲሰጡ የተደረጉ ሲሆን በማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና በስፖርታዊ ውድድሮች የተመዘገቡ ውጤቶች ስኬታማ እንደነበሩ በሪፖርቱ ተመላክቷል። https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.