የከተራ እና የጥምቀት በዓል በሚከበርበት ጃንሜዳ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ ጥር 8 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የከተራ እና የጥምቀት በዓል በሚከበርበት ጃንሜዳ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ ጥር 8 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ወጣት ማህበር ጋር በመተባበር የከተራ እና የጥቅምት በዓል በሚከበርበት ጃንሜዳ የጽዳት ዘመቻ አካሄደ የጥምቀት በዓል ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ በማይዳሰሱ ቅርሶች የተመዘገበ በመሆኑ ከሀገር ውጪ ያሉ በርካታ ቱሪስቶች የሚሳተፉበት በዓል መሆኑን የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብር-ዓለም ደምሴ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ካሏት የአደባባይ በዓሎች አንዱ የሆነው ጥምቀትን ምክንያት በማድረግ በተካሄደው የጽዳት ዘመቻ የተሳፉ የወጣት ማህበር አመራሮች እና ወጣቶችን ምክትል ቢሮ ኃላፊው አመስግነዋል፡፡ የከተማችን ወጣቶች በተደራጀ መልኩ የአካባቢን ሰላም በመጠበቅ እና የሀገራችንን ገፅታ በመገንባት እየተወጡ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው ያሉት አቶ ክብር ዓለም ሁሉም ሰው አከባቢውን መንደሩንና ከተማውን በማጽዳት ለበዓሉ ድምቀት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣት ማህበር ፕሬዘዳነት ወጣት በረከት ቢርቢርሳ በበኩላቸው በዓሉ ላይ በርካታ የከተማችን ወጣች እንደሚሳተፉ ገልጸው ጽዳት ባህል በማድረግ የሚሰሩ ስረዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል በጽዳት ዘመቻው ላይ በጎ ፍቃደኞች፣ የወጣት አደረጃጀቶች፣ የሲቪክ ማህበራት እና የሌሎች ሐይማኖት ተታዮች የተሳተፉ መሆኑን የወጣቶች ንቅናቄና ግንዛቤ ዳይሮክቶሬት ያደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡ https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.