ከ300 በላይ ስፖርኞች የሚሳፉበት የታዳጊ ሰልጣ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ከ300 በላይ ስፖርኞች የሚሳፉበት የታዳጊ ሰልጣኞች ምዘና ውድድር ነገ በ28 ሜዳ ይጀምራል፡፡ ጥር 8 ቀን 2018 ዓ/ም

ከ300 በላይ ስፖርኞች የሚሳፉበት የታዳጊ ሰልጣኞች ምዘና ውድድር ነገ በ28 ሜዳ ይጀምራል፡፡ ጥር 8 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በክቡር ጠቅላይ ሚንስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ኢንሼቲቭ የተጀመረው አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን ግንባታ መሰረት በማድግ ከ300 በላይ ታዳጊ ስፖርተኞች የሚሳፉበት የምዘና ውድድር ጥር 9 ቀን 2018 ዓ/ም በ28 ሜዳ ይጀምራል ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የስፖርት መድረኮች ስሟን ከፍ የሚያደርጉ ተጫዋቾችን የመፍጠር ዓላማ ያደረገ የምዘና ውድድር መሆኑን የገለጹት እንደሚሳፉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ከ300 በላይ የስልጠና ጣቢያዎች ከሚሰለጥኑ ከ7500 በላይ ሰልጣኞች 300 ግልጽና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ መመረጣቸውን ገልጸዋል፡፡ አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን በእግር ኳስ ለመገንባት መሠረት የሚሆኑ ተስጥኦ ያላቸው እና ዕድሜያቸው ከ13 - 15 ብቻ የሆኑ ታዳጊዎች ከ11 ክፍለ ከተማ እና ስፖርት ትምህርተና ስልጠና ማዕከላት መመረጣቸውን አቶ ጎሳዬ አሳውቀዋል፡፡ የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ልማት ለአሸናፊ ብሔራዊ ቡድን ግንባታ በሚል መሪ ቃል 28 ሜዳ በሚካሄደው የታዳጊ ሰልጣኞች ምዘና ውድድር ላይ የፌደራል እና ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በይፋ እንደሚጀምር ተመልክቷል፡፡ https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.