አሸናፊ ብሔራዊ ቡድንን የመገንባት ጉዞ - የታዳ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

አሸናፊ ብሔራዊ ቡድንን የመገንባት ጉዞ - የታዳጊዎች የምዘና ውድድር በአዲስ አበባ ተጀመረ! ጥር 09 ቀን 2018ዓ.ም

አሸናፊ ብሔራዊ ቡድንን የመገንባት ጉዞ - የታዳጊዎች የምዘና ውድድር በአዲስ አበባ ተጀመረ! ጥር 09 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድን “አሸናፊ ብሔራዊ ቡድንን የመገንባት” ራዕይ ከስረ መሰረቱ ለማሳካት፣ ከተማ አቀፍ የታዳጊዎች የእግር ኳስ ምዘና ውድድር በዛሬው ዕለት በደመቀ የመክፈቻ ፕሮግራም አስጀምሯል። በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የቢሮ ሀላፊው አቶ በላይ ደጀን አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን የሚገነባው በአጋጣሚ ሳይሆን በታቀደ እና በሳይንሳዊ መንገድ በሚመራ የታዳጊዎች የሰልጠና ልማት መርሀ ግብር ነው ብለዋል። ዛሬ በከተማ ደረጃ የምናስጀምረው ምዘና ውድድር በስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከላትን ጨምሮ በየክፍለ ከተማው ከሚገኙ 301 የስልጠና ጣቢያዎች ከሚሰለጥኑ 7525 ታዳጊዎች መካከል ከፍተኛ ብቃት ያላቸው 300 ምርጥ ታዳጊዎችን ለይተን የምናካሂደው ነው ብለዋል። አላማችን ስፖርተኛ ማብዛት ብቻ ሳይሆን፣ በቴክኒክ፣ በታክቲክና በአሸናፊነት ስነ-ልቦና የታነጸ ትውልድ በማፍራት ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ ዳግም በክብር ማስጠራት ሲሉ የቢሮ ሀላፊው ተናግረዋል።" ከከተማው ከሚገኙ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዓላማችን ስፖርተኛ ማብዛት ብቻ ሳይሆን፣ በቴክኒክ፣ በታክቲክና በአሸናፊነት ስነ-ልቦና የታነጸ ትውልድ በማፍራት ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ ዳግም በክብር ማስጠራት ነው።" አቶ ዳዊት ትርፉ የቢሮው ምክትል ሀላፊ በበኩላቸው በዚህ የከተማ ደረጃ ምዘና የላቀ ብቃትና ልዩ ተሰጥኦ እንዳላቸው የሚረጋገጥላቸው ታዳጊዎች፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እንዲሁም በከተማ ደረጃ በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አነሳሽነት በሚቋቋሙ የታዳጊዎች ልዩ የሥልጠና ማዕከላት (Elite Centers) ገብተው ዘመናዊና ጥራት ያለው ስልጠና እንዲያገኙ እንደሚደረግ ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ኢ/ር ሀይለእየሱስ ፍስሀ "ይህ የምዘና ሂደት ፍጹም ፍትሃዊና በቴክኒክ ባለሙያዎች የታገዘ ነው። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ታዳጊዎቹን የሚመለምሉ አካላት በቂ ስልጠና እንዲወስዱ ተደርጓል ብለዋል። የምዘና ውድድሩ ጥር 18 ፍፃሜውን የሚያገኝ ሲሆን የፌዴራል እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ይገኛሉ። https://linktr.ee/YouthandSport1

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.