የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ። ጥር12 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ።
ጥር12 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብርን በራስ መተማመን አስፈላጊነት በሚል ርዕስ ተካሄደ
በመርሀ ግብሩ ላይ የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች፣ ጠቅላላ ካውንስል አባላት፣ የፌዴሬሽን ፅ/ቤት ኃላፊዎች እና መላው ሰራተኞች ተገኝተዋል።
ዘውትር ሰኞ ከተማ አስተዳደሩ ባስቀመጠው አቅጣጫ የሚካሄደው መድረክ ካላደር ዝግ በመሆኑ ማክሰኞ መደረጉን የገለጹት የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራ ስራን ውጤታማ ለማድረግ ተቋምን ራዕይ ለማሳካት በዚህ አይነት ርዕስ ሚካሄዱ ውይይቶች ወሳኝ ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የዛሬውን የዐውቀት ሽግግር መረሃ ግብር ያካፈሉት አቶ ገብረ ሕይወት በራስ መተማመን ብያኔ፣ ስለራሰ መተማመንየምሑራን አስተያየት፣በራስ መተማመን ለማሻሻል ስለ ሚሩዱ መንገዶች፣መነሻዎች፣በራስ መተማመን የጎደላቸው ስዎች ችግር ላይ ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡
በራስ መተማመንን ለመገንባት በሚረዱ ጉዳዮች ዝርዝር ማብራርያ የሰጡት አቶ ገብረሕይወት በራስ መተማመን ከፍ በማድረግ ራስን ቤተሰብ እና አገር መለወጥ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.