የ2018 ትምህርት ዘመን የተማሪዎችና መምህራን...

image description
- ውስጥ supporter    0

የ2018 ትምህርት ዘመን የተማሪዎችና መምህራን ስፖርት ሊግ ከተማ አቀፍ ውድድር ማስፈፀሚያ እቅድ እና የውድድር ማካሄጃ ደንቦች ላይ ውይይት ተካሄደ:: ጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የ2018 ትምህርት ዘመን የተማሪዎችና መምህራን ስፖርት ሊግ ከተማ አቀፍ ውድድር ማስፈፀሚያ እቅድ እና የውድድር ማካሄጃ ደንቦች ላይ ውይይት ተካሄደ::

ጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የ2018 ትምህርት ዘመን የተማሪዎችና መምህራን ስፖርት ሊግ ከተማ አቀፍ ውድድር አካሄድን በተመለከተ የውድድር ማስፈፀሚያ እቅድ እና የውድድር ማካሄጃ ደንቦች ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና ወጣቶችና ስፖርት ቢሮዎች ኃላፊዎችና ማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት እና የአዳሪ ትምህርት ቤቶች ርእሳነ መምህራን በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል::

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የተወዳዳሪ ስፖርተኞች መፍለቂያ ትምህርት ቤቶች መሆናቸውን ገልፀው የ2018 ትምህርት ዘመን የተማሪዎችና መምህራን ስፖርት ሊግ ውድድር በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል::

ዶክተር ዘላለም የስፖርት ሊግ ውድድሩ ተማሪዎች እርስ በርስ እንዲወዳጁ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረው በቀጣይ በከተማ ደረጃ የሚኖሩ የተማሪዎችና የመምህራን ስፖርት ሊግ ውድድሮች ያማሩና የደመቁ ፤ ጠንካራ ፍክክር የሚታይባቸውና ስፖርታዊ ስነምግባርን የተከተሉ እንዲሆኑ ልንሰራ ይገባል ብለዋል:: አያይዘውም ውድድሩ ተማሪዎችን ለበለጠ ስራ እንዲነሳሱና በትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር ባህል ሆኖ እንዲቀጥል የራሱ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን ገልፀው ውድድሩ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ በቀጣይ ስፖርታዊ ውድድሩ በሚካሄድበት ወቅት ሊተገበሩ የሚገባቸው ተግባራት እና የስነምግባር ላይ በትኩረት እንዲሰራ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል::

የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በበኩላቸው የትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድሮች ወንድማማችነትን የምናጠናክርበትና ተተኪ ስፖርተኞችን የምናፈራበት ነው ብለው ከባለፈው ዓመት ስፖርት ውድድር የተሻለ ውድድር ለማካሄድ በውድድሩ ላይ የሚካሄዱ ጨዋታዎች በታቀደው መሰረት ደንብና መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት ለማካሄድ የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል::

በውይይቱ የተማሪዎችና መምህራን ስፖርት ሊግ ውድድር ማስፈፀሚያ እቅድ እና የውድድር ማካሄጃ ደንቦች ላይ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል::

https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.