የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ባለፉት አምስት የለውጥ ዓመታት አፈጻጸም ዙሪያ ከአመራሮች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ ጥር 14 ቀን 2018ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ባለፉት አምስት የለውጥ ዓመታት አፈጻጸም ዙሪያ ከአመራሮች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ ጥር 14 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ባለፉት አምስት የለውጥ ዓመታት በዘርፉ የተከናወኑ አበይት ተግባራትን አስመልክቶ ከክፍለ ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊዎች፣ ከአዲስ አበባ ከወጣት ማህበር፣ ወጣት አደረጃጀትና ወጣት ክንፍ አመራሮች ጋር ሰፊ ውይይት አካሂዷል። በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን እንደገለጹት፤ ባለፉት አምስት የለውጥ ዓመታት የከተማዋን ወጣቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የስፖርት ዘርፉን ለማነቃቃት ስትራቴጂካዊ ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልፀዋል። ኃላፊው አክለውም "ለውጡ የወጣቶችን የመሪነት ሚና ከማሳደግ ባለፈ፣ በከተማዋ ሰላምና ልማት ላይ ያላቸውን አሻራ በጉልህ እንዲያርፉ አስችሏል" ብለዋል። ባለፉት አምስት የለውጥ ዓመታት የአዲስ አበባ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ በአቅመ ደካሞች ቤት እድሳትንና በልማት ስራዎች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን፣ በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በተዘዋዋሪ ፈንድ አቅርቦትና በኢንተርፕራይዞች አደረጃጀት ሰፊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የማረጋገጥ፤ በተያያዘም ወጣቶች በውሳኔ ሰጭነት ደረጃ እንዲሳተፉና በመሪነት ሚና ላይ እንዲመጡ በማድረግ ረገድ የተሰሩ ስራዎች የፖለቲካ ተሳታፊነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የተሰሩ ስራዎች በውይይት መድረኩ በስፋት ተነስተዋል። የመዲናዋን ስፖርት ሁለንተናዊ ልማት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ደረጃውን የጠበቁ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ፣ የታዳጊዎችና ወጣቶች ስልጠና፣ የስፖርት ማህበራትን ማጠናከር እና ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት፣ እንዲሁም ስፖርት ለሁሉም ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች ባለፉት የለውጥ አመታት ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን በውይይቱ ተመላክቷል። የመድረኩ ተሳታፊ አመራሮች በበኩላቸው፤ የተመዘገቡ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና የታዩ ክፍተቶች በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ውስጥ ተካተው እንዲፈጸሙ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል። በመጨረሻም የቢሮ ኃላፊው በሰጡት ማጠቃለያ፤ የከተማዋን ወጣቶች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግና አዲስ አበባን የስፖርት ማዕከል ለማድረግ አመራሩ በቁርጠኝነትና በቅንጅት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል። ለበለጠ መረጃ https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.