በአስር አመታት ውስጥ አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል የተባለ የስፖርት ሜዳ ግንባታ ተጀመረ።
በአስር አመታት ውስጥ አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል የተባለ የስፖርት ሜዳ ግንባታ ተጀመረ። ጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 1 ወጣቶች ጊዜያቸውን የሚያሳልፉበት፣ አካላዊና አዕምሯዊ እድገታቸውን የሚገነቡበት እና በአስር አመታት ውስጥ አሸናፊ ቡድን ለመገንባት ሀገሪቷ በምታደርገው ጥረት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል የተባለ ዘመናዊ የስፖርት ሜዳ ግንባታ የከተማና የክ/ከተማ እንዲሁም የወረዳ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት ተጀመረ። የመደመር መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራባቸው ከሚገኙ ተግባራት ውስጥ አንዱና ዋነኛው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይቶ መፍታት መሆኑን የገለጹትና በተለይም ለወጣቶችና ህጻናት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ በአዲስ አበባ ውስጥ ብቻ ባለፉት 7 አመታት ከ1547 በላይ ስፖርት ማዘውተሪያዎች ከሌሎች የልማት ስራዎች ጋር ተስማምተው እንዲገነቡ መደረጉን የገለጹትና በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በዛሬው እለትም የተጀመረው የስፖርት ማዘውተሪያ የወጣቶች የዘመናት ጥያቄ እንደነበር ገልጸው በዚህም የበርካታ ወጣቶችን ህይወት ማሻሻል የሚያስችል ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። በዛሬው እለት ግንባታው የተጀመረው የስፖርት ማዘውተሪያ ሲጠናቀቅ የበርካታ ወጣቶችን ስብእና ለመገንባት ያስችላል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ያሉት የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ኡመር የከተማ አስተዳደሩ ከተማዋን ውብ፣ ጽዱና ምቹ ለማድረግ በሰራው ስራ በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረጉን ገልጸዋል። አክለውም በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባሩ እንዲጠናቀቅ የአካባቢው ወጣቶችና ነዋሪዎች አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ አቶ ወንድሙ መልዕክት አስተላልፈዋል። የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 1 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መንገሻ ሲሳይ በበኩላቸው መንግስት በርካታ ሰው ተኮር ስራዎችን በመስራት ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገና የከተማዋንም ደረጃ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እያደረገ መሆኑን ገልጸው በዛሬው እለት ግንባታው የተጀመረው የስፖርት ማዘውተሪያ የወጣቶችን ስብዕና ከመገንባትም ባለፈ ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ከመፍጠር አንጻር የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። ግንባታውን በአጭር ጊዜ አጠናቆ ለአገልግሎት ብቁ ለማድረግ ሌት ተቀን የሚሰራ መሆኑ ተገልጿል። አራዳ ኮሙኒኬሽን
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.