ከተማ አቀፍ የታዳጊ ሰልጣኞች ምዘና ውድድር እን...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ከተማ አቀፍ የታዳጊ ሰልጣኞች ምዘና ውድድር እንደቀጠለ ነው ለዋንጫ ለማለፍ ቦሌ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ፤ኮልፌ ከአዲስ ከተማክፍለ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

ከተማ አቀፍ የታዳጊ ሰልጣኞች ምዘና ውድድር እንደቀጠለ ነው

ለዋንጫ ለማለፍ ቦሌ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ፤ኮልፌ ከአዲስ ከተማክፍለ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

ጥር 14 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በክቡር ጠቅላይ ሚንስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ኢንሼቲቭ የተጀመረው አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን ግንባታ መሰረት በማድረግ ከ300 በላይ ታዳጊ ስፖርተኞች እየተሰተፉበት የሚገኘው የታዳጊዎች ምዘና ውድድር እንደቀጠለ ነው፡፡

ቅዳሜ ለዋንጫ ለማለፍ በ24 ሜዳ ቦሌ ከነፋስ ስልክ አጓጊ ጨዋታ ሲደርጉ ኮልፌ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚያደርጉት የእግር ኳስ ውድድር ተጠባቂ ነው፡፡

ቀጣይ አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን በእግር ኳስ ለመገንባት መሠረት የሚሆኑ ተስጥኦ ያላቸው ታዳጊ ስፖርተኞችን የመለየት ስራ በጥንቅ ዲስፕሊን እና በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ አለማየሁ ገልጸዋል፡፡

አሸናፊ ብሔራዊ ቡድንን የመገንባት ጉዞ የታዳጊዎች የምዘና ውድድር ላይ አስረ አንዱም ክፍለ ከተማ እየተሳተፉ የገለጹት አቶ ጎሳዬ በስመ ጥር የእገር ኳስ ባለሙያዎች የሚለዩ ተተኪ ስፖርተኞች በአገር አቀፍ እና በከተማ ደረጃ ታቅፈው ልዩ ስልጠና እንደሚወስዱ ጠቁመዋል፡፡

በውድድሩ የምድብ ሀ ምርጦች ቦሌ እና ነፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ 1ኛ እና 2ኛ ሲወጡ፣ ባገኙት ነጥብ ከምድብ ለ ኮልፌ 1ኛ ምድብ ሐ 1 አዲስ ከተማ ክፍለ ወደ ቀጣይ ምርጥ አራት ውስጥ ገብተዋል፡፡

በለቡ ሙዚቃ ሰፈር በሚገኘው ስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ እሁድ የዋንጫ እና የደረጃ ጨዋታዎች እንደሚካሄዱ ተመልክቷል

https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.