በልደታ ክፍለ ከተማ በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከል የሚገኝን የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ መልሶ ለማለት የሚያስችል የስምምነት ፊርማ ተካሄደ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ/ም
በልደታ ክፍለ ከተማ በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከል የሚገኝን የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ መልሶ ለማለት የሚያስችል የስምምነት ፊርማ ተካሄደ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከታን ኢንጂነሪንግ በጋራ በመሆን በክፍለ ከተማው በወረዳ 08 ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከል የሚገኘውን ሜዳ ለማስዋብ የሚያስችል የሁለትዮሽ የፊርማ ሥነ ስርዓት አካሄዱ። የፊርማ ሥነ ሥርዓቱ በማዕከሉ የሚገኘውን ሜዳ መልሶ በማልማት ምቹ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት መሆኑ ተመልከቷል፡፡ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ 114 የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላትን ሳቢ እና ማራኪ ለማድረግ በራስ አቅም በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ የገለጹት ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ክብር ዓለም ደምሴ ከታን ኢንጂነሪግ ጋር በተደረገው ስምምነት የሚሰራው ሜዳ ደራጀውን የጠበቀ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ማዕከላቱ ለወጣቶች አዕምሯዊ፣ አካላዊና ስነ-ልቡናዊ እድገት ላይ የጎላ ሚና እየተጫወቱ እንደሚቻል ያስታወሱት አቶ ክብርዓለም የወጣቶች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሚሰሩ አካላት በቅርበት የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡ የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ በበኩላቸዉ በክፍለ ከተማው በሚሰራው ሜዳ እስኪጠናቀቅ በተቀናጀ መንገድ አስፈላጊው ክትትል እንደሚደረግ ገልጸው ግንባታው ዕውን ሲሆን የወጣት ስብዕና ማዕከላትን አቅም እንደሚያጠናክር ገልጸዋል https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.