ማዕከላት ወጣቶችን በአጫጭር ስልጠናዎች እያበቁ...

image description
- ውስጥ supporter    0

ማዕከላት ወጣቶችን በአጫጭር ስልጠናዎች እያበቁ እንደሚገኝ ተገለጸ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣች እና ስፖርት ቢሮ

ማዕከላት ወጣቶችን በአጫጭር ስልጠናዎች እያበቁ እንደሚገኝ ተገለጸ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣች እና ስፖርት ቢሮ የወጣት ሰብዕና መገንቢያ ማዕከላት ወጣቶችን በአጫጭር ስልጠናዎች በማብቃት የስራ ዕድል እየፈጠሩ እንደሚገኝ ተገለጸ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከል ከአይ ኬር ፎር ዘኔሽን አገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር በጥፍር ስራ፣ በሜካፕ፣ በፀጉር ስራ፣ በልብስ ስፌትና ምግብ ዝግጅት ለወራት ያሰለጠናቸውን ወጣቶች አስመርቋል። በማዕከሉ በተግባር እና በንደፋ ሃሳብ የተደገፈውን የሙያ ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች መንግስታዊ ባልሆኑና በግል ድርጅቶች የሥራ እድል የሚያገኙበት ሰፊ እድል መኖሩን የወረዳ 6 ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የስራና ክህሎት ጽቤት ኃላፊ አቶ ፈልመታ ቦጋለ ገልጸዋል ስልጠናው ተከታትለው ያጠናቀቁ ወጣቶች ተደራጅተው የመስሪያ ቦታ እንደሚመቻእላቸው ያበሰሩት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው የስራ አጥነት ችግርን ለማቃለል ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ባለመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ቢሮው የወጣቶችን የሥራ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የተግባርና የጽንሰ ሀሳብ ስልጠናዎችን በቅንጅት እየሰጠ እንደሚገኝ የወጣቶች ማብቃት ዳይሮክቶሬት ያደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡ https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.