ቢሮው በኢጣልያን የገንዘብ ድጋፍ ያስገነባውን የ...

image description
- ውስጥ supporter    0

ቢሮው በኢጣልያን የገንዘብ ድጋፍ ያስገነባውን የወጣቶች ሙያ ማሰልጠኛ ባለ አራት ወለል ሕንጻ አስመረቀ። ጥር 16 ቀን 2018 ዓ/ም

ቢሮው በኢጣልያን የገንዘብ ድጋፍ ያስገነባውን የወጣቶች ሙያ ማሰልጠኛ ባለ አራት ወለል ሕንጻ አስመረቀ። ጥር 16 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በኢጣልያን ኮርፕሬሽን የገንዘብ ድጋፍ ያስገነባው የወጣቶች ሙያ ማሰልጠኛ ባለ አራት ወለል እና ሕንጻ ተመረቀ ፊኒክስ የስራ ላብራቶሪ የተሰኘው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ወጣት ሰብዕና መገንቢያ ማዕከል የተገነባው ህንጻ ወጣቶችን እና አቅመ ደካሞችን በሙያ ስልጠና ለማብቃት ታስቦ የተገነባ ሲሆን የቆዳ ውጤቶችን ጨምሮ የልብስ እና የጸጉር መስሪ ቦታዎቸ ከነ ሙሉ እቃው የተሟሟላት መሆኑ ተመልክቷል በምረቃ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብር-ዓለም ደምሴ የህንጻው ግንባታ ለወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር የከተማዋን ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንደሚፋጥን ገልጸዋል፡፡ በኢጣልያ የገንዘብ ድጋፍ በኢል ሶል የተተገበረው ባለ አራት ወለል ህንጻ ወጣቶችን በልብስ ስፌት፣በቆዳ ውጤቶች፣ በሴቶች እና በወንዶች የጸጉር ውበት፣በምግብ ቤት ራሳቸውን ችለው አገራቸውን ለመጥቀም እንደሚስቻላቸው የኢል ሶል የኢትዮጵያ ተጠሪ ኒኪ ፒሮንቲ ገልጸዋል፡፡ የአሜን ተወካይ ፓስተር ፍራንኮ ሮቬሊያ በበኩላቸው ድርጅታቸው ወጣቶችን ለማነጽ በቅንጅት የተሰራው ስራ ውጤታማ መሆኑን አውስተው አገርን ለማበልጸግ ወጣቶች ላይ መስራት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.