የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በተለ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 190 ወጣቶችን አስመረቀ ጥር 16 ቀን 2018 ዓ/ም ወ

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 190 ወጣቶችን አስመረቀ ጥር 16 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከኢጣልያን ኮርፕሬሽን እና ከኢል ሶል ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ለተከታታይ ስድስት ወር በጋርመነት፣ በጸጉር ስራ እና በሌሎች ሙያዎች ያሰለጠናቸውን ከ180 በላይ ወጣቶች አስመረቀ፡፡ በልደታ ማኒፋክቸሪንግ ኮሌጅ ላለፉት ስድስት ወራት በልብሰ ስፌት፣ በጸጉር ስራ እና በልዩ ልዩ ሞያዎች የሰለጠኑ ወጣቶችን የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብርዓለም ደምሴ፣ የኢል ሶል ተጠሪ ኒኪታ ፒሮንቲ፣ የአሜን ተወካይ ፓስተርን ፍራንኮ ሮቬልያ በተገኙበት በይፋ ተመርቀዋል፡፡ ዛሬ የተመረቁ ወጣቶች ከራስ አልፈው ቤተሰብን አገርን የማገዝ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው የገለጹት አቶ ክብረዓለም የወጣቶችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ለወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራን ለማስፈፋት መንግስት ከሚያደርገው ዘርፈ ብዙ ጥረት ባለፈ መንግስታዊ ያልሆኑ አገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው የገለጹት አቶ ክብር-ዓለም ተማረቂዎች ያገኙትን ዕድል ወደ ውጤት በመቀየር የድርጅቱን ፍሬያማነት እንዲያስቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ተመራቂዎቹ ላለፉት ስድስት ወራት ቴክኒካል ስልጠና በምግብ፣ በጸጉር ስራ በለቱም ጾታ፣ በልብስ ስፌት እና በሌሎች ዘርፎች በቂ ስልጠና መውሰዳቸውን የገለጹት የኢል ሶል የኢትዮጵያ ተጠሪ ኒኪ ፒሮንቲ በጣሊያን የገንዘብ ድጋፍ ከ180 በላይ ወጣቶችን ከማስመረቅ ባሻገር የስራ ዕድል እንደሚፈጠርላቸው አስታውቀዋል፡፡ የነገ ወጣቶችን ለማጠናከርና ውጤታማ ለማድረግ ከልደታ ማኒፋክቸርኒግ ጎሌጅ ከንፋስ ስልክ እና ከምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ኒኪታ ገልጸዋል ወጣቶች የአገር ግንቢ ናቸው ያሉት የአሜን ተወካይ ፓስተር ፍራንኮ ሮቬሊያ ሁሉም ወጣቶች የስራ ዕድል እንዲያገኙ እና እንዲለወጡ በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በምርቃት መርሀ ግሩ ላይ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ድርጅቶችን እና ግለሰቦች ቢሮው ዕውቅና መስጠቱ ተመልክቷል፡፡ https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.