ባካሪ ሳኛ በአዲስ አበባ፡ ከአድዋ መታሰቢያ እስ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ባካሪ ሳኛ በአዲስ አበባ፡ ከአድዋ መታሰቢያ እስከ ስፖርት ሜዳዎች! ጥር 18 ቀን 2018ዓ.ም

ባካሪ ሳኛ በአዲስ አበባ፡ ከአድዋ መታሰቢያ እስከ ስፖርት ሜዳዎች! ጥር 18 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የቀድሞው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን እና የአርሰናል ዝነኛ ተከላካይ ባካሪ ሳኛ በአዲስ አበባ የሚያደርገውን ጉብኝት ዛሬም ቀጥሎ ይውላል። በትላትናው እለት የአዲስ አበባን አዲስ ገጽታ የሚያሳየውን እና የአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌት የሆነውን ግዙፉን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እና ውቡን አንድነት ፓርክን ጨምሮ ሌሎች የልማት ስራዎችን መጎብኝቱ ይታወቃል። ሳኛ በከተማዋ ለውጥና በታሪካዊ ስፍራዎቹ መደመሙን ገልጿል። ዛሬ ደግሞ ሙሉ ትኩረቱን ወደ ስፖርቱ በማድረግ በከተማዋ እየተገነቡና አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የስፖርት መሰረተ ልማቶችን ተዘዎውሮ የሚመለከት ሲሆን ነገ የሀገራቸውን ስም ለሚያስጠሩ ታዳጊ ስፖርተኞች በማግኝት ልምዱን የሚያካፍልም ይሆናል። ይህ ጉብኝት ለኢትዮጵያ ስፖርት እድገትና ለታዳጊዎች መነሳሳት ትልቅ ትርጉም ያለው ነው። https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.