ወጣትነት በሱሰኝነት አይታሰርም!" - በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
ወጣትነት በሱሰኝነት አይታሰርም!" - በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
ጥር 20 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ ወጣቶች ያዘጋጀው የአሉታዊ መጤ ልማዶችና የአደንዛዥ እፅ መከላከያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።
መድረኩ በዘርፉ የረጅም ጊዜ የሙያ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የታገዘ ስልጠና የተሰጠበት ሲሆን፣ ወጣቶች ከሱሰኝነት ወጥመድ ራሳቸውን እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸውና ለሌሎችም አርአያ መሆን በሚችሉባቸው መንገዶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በስልጠናው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ክብረአለም ደምሴ ወጣትነት የፈጠራ፣ የጥንካሬና የህልም ጊዜ እንጂ በሱሰኝነትና በማንነት ቀውስ የሚባክን ሊሆን አይገባም ሲሉ ተናግረዋል።
በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ የተገኙ ወጣቶች ከሱሰኝነት ራስን ከመከላከል ባለፈ፣ በየክፍለ ከተማችው ለሚገኙ እኩዮቻችወ አርአያና የግንዛቤ አምባሳደር እንዲሆኑ አቶ ክብረ አለም አሳስበዋል።
በመድረኩ ላይ ልዩ ትኩረት የሳበው ሱሰኝነት ተጽዕኖን ተቋቁሞ የወጣው የወጣት ዮናታን ምስክርነት ሲሆን ወጣት ዮናታን ሱሰኝነት በህይወቱ ላይ ያደረሰውን ውድቀትና ካገገመ በኋላ ያገኘውን አዲስ ተስፋ ለወጣቶቹ በዝርዝር አጋርቷል።
በመጨረሻም፣ ሰልጣኝ ወጣቶች መሰል መድረኮች በየክፍለ ከተማውና በየወረዳው ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.