2ኛው የከተማ አቀፍ የተማሪዎች ስፖርት ሊግ እና...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

2ኛው የከተማ አቀፍ የተማሪዎች ስፖርት ሊግ እና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር " ቅዳሜ ይጀመራል! ጥር 21 ቀን 2018 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

2ኛው የከተማ አቀፍ የተማሪዎች ስፖርት ሊግ እና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር " ቅዳሜ ይጀመራል!

ጥር 21 ቀን 2018 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ድብቅ ተሰጥኦዎችን በማውጣት የአሸናፊ ብሔራዊ ቡድን ግንባታን ለማገዝ ያለመው 2ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎች ስፖርት ሊግ እና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር ቅዳሜ ጥር 23 አበበ ቢቂላ ስታድየም ይጀምራል።

ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በጋራ ውድድሩን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

"በአካል ብቁና በአእምሮ ንቁ ትውልድ ለሀገር ብልፅግና!" በሚል መሪ ቃል ውድድሩ የሚካሄድ ሲሆን ትምህርት ቤቶች የተተኪ ስፖርተኞች ዋነኛ መፍለቂያ ተቋማት እንዲሆኑ ለማድረግና ለሀገር ደረጃ የሚተርፍ አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት በታለመው ስትራቴጂ ውስጥ ትልቅ ድርሻ እንዳለው በመግለጫው ተገልፆል።

ውድድሩ ለ15 ተከታታይ ቀናት በከተማው በሚገኙ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የሚካሄድ ሲሆን የእግር ኳስ ስፖርትን ጨምሮ በ12 የስፖርት አይነቶች በሶስት ካታጎሪ ውድድሩ የሚካሄድ ይሆናል ።

2ኛው የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድሩ ከትምህርት ቤቶች ጀምሮ በወረዳ እና በክፍለ ከተማ ደረጀ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን በአጠቃላይ ከ30ሺህ በላይ ስፖርተኞች ተሳታፊ መሆናቸው ተመላክቷል።

https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.