በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መተዳደሪያ ደንብ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መተዳደሪያ ደንብ እና የክፍያ ተመን አተገባበር ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ ጥር 21 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መተዳደሪያ ደንብ እና የክፍያ ተመን አተገባበር ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

ጥር 21 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ የተገነቡ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መተዳደሪያ ደንብ እና የክፍያ ተመን አተገባበር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት አካሄደ።

በመድረኩ ላይ የቢሮው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ የ11ዱም ክፍለ ከተማ እና የወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊዎች፣ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ስራ አስኪያጆች እንዲሁም የስፖርት ማህበራት ስራ አስፈፃሚዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች የተከናወነውን የማዘውተሪያ ስፍራዎች አጠቃቀም የደንብ እና የክፍያ ተመን አተገባበር የኢንስፔክሽን ሪፖርት ቀርቧል።

በሪፖርቱም በአንዳንድ ክፍለ ከተሞች በወጣው ደንብና የክፍያ ተመን መሠረት ካለመስራት ጋር ተያይዞ የአፈጻጸም ክፍተቶች መኖራቸው የተጠቆመ ሲሆን፣ በተለይም ደንቡን እና የክፍያ ተመኑን ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ግንዛቤ ከመፍጠር አኳያ መዳከሞች መኖራቸው በውይይቱ ላይ ተነስቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የመተዳደሪያ ደንቡና የክፍያ ተመኑ የወጣው የአሰራር ግልጽነትን ለመፍጠርና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ መሆኑን ገልጸዋል።

አተገባበሩ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ቢሮው በቁርጠኝነት እንደሚሰራ የገለጹት ሀላፊው፣ በቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች የሰጡ ሲሆን

ሁሉም ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች በከተማ አስተዳደሩ በወጣው መተዳደሪያ ደንብና የክፍያ ተመን መሠረት ብቻ እንዲሰሩና ከዚህ ውጭ የሚደረጉ ማናቸውም አሰራሮች በአስቸኳይ እንዲቆሙ፤

ስለ ደንቡና የክፍያ ተመኑ ለሚመለከታቸው አካላትና ለሰፊው ተጠቃሚ ህዝብ ጥልቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እንዲከናወኑ፤

ደንቡንና አሰራሩን ጥሰው በሚገኙ አካላት ላይ ጥብቅ የክትትልና የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ ተጠያቂነት እንዲሰፍን፤

ማዘውተሪያ ስፍራዎቹ ያለ ምንም አድልዎ ለወጣቱና ለስፖርት ቤተሰቡ በፍትሃዊነት አገልግሎት እንዲሰጡ ክትትል እንዲደረግ አሳስበዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት መድቦ የገነባቸው እነዚህ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉና ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ የደንቡ መከበር ወሳኝ መሆኑ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ተገልጿል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የክፍለ ከተማ ኃላፊዎችና የማዕከላት ስራ አስኪያጆች በበኩላቸው፤ ደንቡን ተግባራዊ ለማድረግና የታዩ ክፍተቶችን ለማረም ያላቸውን ዝግጁነት ገልፀዋል።

https://linktr.ee/YouthandSport1

+5

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

457Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 455 ሌሎች

103

45

ይውደዱ

አስተያየት

ያጋሩ

ተጨማሪ አስተያየቶችን ይመልከቱ

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.