የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖ...

image description
- ውስጥ supporter    0

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች አጠቃቀም ደንብና የክፍያ ተመን አተገባበር ላይ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ወጣቶችን ጨምሮ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር እየመከረ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች አጠቃቀም ደንብና የክፍያ ተመን አተገባበር ላይ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ወጣቶችን ጨምሮ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር እየመከረ ነው።

ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ያፀደቀውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መተዳደሪያ ደንብ እና የክፍያ ተመን አተገባበርን በተመለከተ ከቢሮ ሰራተኞች እና የከተማው ወጣቶችን ጨምሮ ከ11ዱም ክክፍለ ከተማ ከሚገኙ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ሰፊ የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

በውይይት መድረኩ በከተማዋ የሚገኙ የስፖርት መሰረተ ልማቶችን ለህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግና አጠቃቀማቸውንም ግልፅ በሆነ አሰራር ለመምራት በሚያስችሉ ነጥቦች ላይ ውይይት ተደርጓል።

ከቢሮው ሰራተኞቻ ጋር በተካሄደው ውይይት ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ባስተላለፉት መልዕክት፤ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የከተማዋ ስፖርት የሚገነባባቸውና ወጣቶች ክህሎታቸውን የሚያሳድጉባቸው ስፍራዎች በመሆናቸው፣ አጠቃቀማቸው በህግና በስርአት ሊመራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

መተዳደሪያ ደንብና የክፍያ ተመን ተግባራዊ መደረጉም የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎቹ በፍትሃዊነትና በግልፅነት ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ ለማድረግ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።

በመድረኩ ላይ በ11ዱም ክፍለ ከተማ በተካሄደው የኢንስፔክሽን ስራ የተገኙ ግኝቶችና የሪፖርት ሰነድ በአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ብርሀኑ ባዩ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ይህ የኢንስፔክሽን ሪፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎቹ በአሁኑ ወቅት ያሉበትን ተጨባጭ ሁኔታና በቀጣይ መስተካከል ያለባቸውን የአሰራር ክፍተቶች በዝርዝር ያመላከተ መሆኑ ተጠቅሷል።

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ያፀደቀው ይህ ደንብና የክፍያ ተመን፣ ስፖርትን በከተማ ደረጃ ለማሳደግና የማዘውተሪያ ስፍራዎችን በዘላቂነት ለመጠበቅና ለማልማት እንደሚያግዝ በውይይቱ ወቅት ተመላክቷል።

ቢሮው ይህንን አሰራር በሁሉም ክፍለ ከተሞች እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ተግባራዊ ለማድረግ የክትትልና ድጋፍ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ ሚሊዮን ኮራን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራን ገልጿዋል።

በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች አጠቃቀም ላይ ያለውን አስተያየትና ጥያቄ በዘላቂነት ለመመለስ በቴክኖሎጅ የታገዘ አገልግሎት ለመስጠት በቀጣይ ቢሮው ትኩረት ረጥቶ እንደሚሰራ አቶ ሚሊዪን አሳውቀዋል።

https://linktr.ee/YouthandSport1

+7

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

230You፤ Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 227 ሌሎች

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.