በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በአገልግሎት ክፍያ ዙሪያ በተዘጋጀ የማስፈፀሚያ መመሪያ ሰነድ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ። ጥር 22 ቀን 2ዐ18ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በአገልግሎት ክፍያ ዙሪያ በተዘጋጀ የማስፈፀሚያ መመሪያ ሰነድ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።
ጥር 22 ቀን 2ዐ18ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገነቡ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በአገልግሎት ክፍያ በከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በተወሰነ የማስፈፀሚያ መመሪያ ሰነድ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሄዳዷል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳዊት ይፍሩ ከለውጡ በፊት በነበረው ስርዓት የነበሩ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ወደ አራት መቶ የሚጠጉ ነበር አሁን ግን የለውጡ መንግስት ከመጣ በኋላ የሰው ተኮር ስራዎችን በመሠራቱ እንዲሁም ማህበረሰቡ በስፖርት ማዘውተሪያ አስፈላጊነት ግንዛቤ በማደጉ ከነበረው ወደ አራት እጥፍ ማሳደግ ተችሏል ያሉት አቶ ዳዊት ከተማችን በከፍተኛ የለውጥ ፍጥነት ውስጥ በመሆኗ በነበሩ የልማት ስራዎች ጋር ተያይዞ የተሠሩ ማዘውተሪያ ስፍራዎች መተዳደሪያ ደንብ ማውጣት አስፈልጓል ሲሉ ለመመሪያው ተፈፃሚነትም የሚመለከተው አካል አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ ይኖርበታል ሲሉም ተናግረዋል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ዝናቤ በበኩላቸው የዚህ መመሪያ መዘጋጀት በዋናነት አላማው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ እና ሸጣይነት እንዲኖራቸው በማድረግ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተመጣጣኝ በሆነ ክፍያ በእኩልነትና በፍትሐዊነት አገልግሎት መስጠት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የለሚ ኩራ ኮሙኒኬሽን
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.