2ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎች ስፖርት ሊግ እና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር በዛሬው ዕለት ተጀመረ ጥር 23 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
2ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎች ስፖርት ሊግ እና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር በዛሬው ዕለት ተጀመረ
ጥር 23 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
"በአካል ብቁና በአእምሮ ንቁ ትውልድ ለሀገር ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 2ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎች ስፖርት ሊግ እና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር ዛሬ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታድየም በድምቀት ተጀምሯል።
በመክፈቻው ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ባስተላለፉት መልዕክት፣ ውድድሩ የወጣቶችን ስፖርታዊ ክህሎት ከማሳደግ ባለፈ ጤናማና አምራች ዜጋን ለመቅረጽ ያለውን ፋይዳ ገልጸዋል።
የውድድሩ ዋነኛ ትኩረት ትምህርት ቤቶችን የተተኪ ስፖርተኞች መፍለቂያ ተቋማት ማድረግ መሆኑን የገለፁት አቶ በላይ በቀጣይ 10 ዓመታት እንደ ሀገር አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን የመገንባት ግብ ለማሳካት ትምህርት ቤቶች ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው፣ ትምህርትና ስፖርት ተመጋጋቢ መሆናቸውን በመጥቀስ፤ ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል
መምህራን በውድድሩ መካተታቸውም በትምህርት ማህበረሰቡ መካከል ያለውን ትስስር ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ዶ/ር ዘላለም ገልጸዋል።
በትምህርት ቤቶች የሚገኙ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ከትምህርት ማህበረሰቡ በተጨማሪ የአከባቢው ማህበረሰብ እንዲጠቀምባቸው ክፍት እንደሚሆኑ ሀላፊው አሳውቀዋል።
ውድድሩ ከዛሬ ጥር 23 ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በሚቆየው በዚህ ታላቅ ስፖርታዊ መድረክ፤ ከየክፍለ ከተማው የተውጣጡ ተማሪዎችና መምህራን ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን፣ የእግር ኳስ ስፖርትን ጨምሮ በ12 የተለያዩ የስፖርት አይነቶች ውድድሮች እንደሚካሄዱ ታውቋል።
https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.