የ"5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ" ስልጠና የላቀ አስ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

የ"5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ" ስልጠና የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ዕውቅና ተሰጠ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የ"5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ" ስልጠና የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ዕውቅና ተሰጠ

ጥር 23 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

አዲስ አበባ ከተማ በቴክኖሎጂ የታገዘ ኢኮኖሚ ለመገንባት በምታደርገው ጉዞ ላይ በ"5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ" ስልጠና ወሳኝ ሚና ለተጫወቱ ክፍለ ከተሞች ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት እና ወጣቶች ዕውቅና ተቸራቸው

ወጣቱን በዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግና የከተማ አስተዳደሩን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ትግበራ ለማፋጠን የተሰራው ስራ ውጤታማ መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብር-ዓለም ደምሴ ስልጠናውን በብቃት ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ለዲጂታል ኢኮኖሚ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያመጡ ጥሪ አቅረበዋል፡፡

ከ62 ሺህ በላይ ወጣቶች ስልጠናውን መውሰዳቸውን የገለጹት አቶ ክብርዓለም አስፈላጊውን የኮዲንግ ዕውቀት የቀሰሙ ወጣቶች ስልጠናውን መውሰድ ብቻ ሳይሆን በየቀኑ መለማመድና ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡

በዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች መጠቀምን አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ያመላከቱት አቶ ክብር ዓለም የዕውቅናው ዓላማ በክፍለ ከተሞች እና በወጣት ሰብዕና መገንቢያ ማዕከላት መነቃቃት ለመፍጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዕውቅና መረሃ ግብሩ ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወጣቶችን ያሰለጠኑ ክፍለ ከተሞች ለሳይንስ ካፌ ልዩ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ወጣቶች፣ስልጠናዉን ሰልጥነው ያሰለጠኑ ወጣቶች፣ የላቀ አፈጻጸም ያላቸው ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት እና የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ክፍለ ከተሞች እውቅና ተችሯል፡፡

በዕውቅና መርሃ ግብሩ ላይ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እና ቦሌ ክፍለ ከተማ የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገባቸው የዴስክ ቶፕ ኮምፒዩተር ተበርክቶላቸዋል፡፡

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.