ተተኪ ስፖርተኞችን የማፍራቱ ብሔራዊ ጉዞ በአዲስ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ተተኪ ስፖርተኞችን የማፍራቱ ብሔራዊ ጉዞ በአዲስ አበባ ለ15 ቀናት ሲካሄድ ቆይቷ ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል። ጥር 24 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ሰፖርት ቢሮ

ተተኪ ስፖርተኞችን የማፍራቱ ብሔራዊ ጉዞ በአዲስ አበባ ለ15 ቀናት ሲካሄድ ቆይቷ ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል።

ጥር 24 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ሰፖርት ቢሮ

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ኢንሼቲቭ የተጀመረውና ጠንካራ ተተኪ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት ያለመው የተተኪ ስፖርተኞች ምልመላ ፕሮግራም ለ15 ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በማጠቃለያ ላይ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ይህ የምልመላ መርሃ ግብር ከተማዋ ለጀመረችው ሰፊ የስፖርት ልማት ስራ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል። "አሁን በምልመላው የተለዩ 45 ታዳጊዎች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴሩ እና በክብርት ከንቲባዋ በሚቋቋመው ልዩ የሥልጠና ፕሮጀክት መታቀፋቸው፣ የሀገራችንን ስፖርት ከዝምባሌ ባለፈ በሳይንሳዊ እና በተቋማዊ መንገድ ለመምራት የተጀመረው ጉዞ አካል ነው" ብለዋል።

በከተማዋ እየተገነቡ ያሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችና የኮሪደር ልማት ስራዎች ለነዚህ ተተኪ ስፖርተኞች ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥሩ ጠቁመው፤ "የከተማዋ ስፖርት እንዲያድግ መሰረተ ልማት ብቻ ሳይሆን፣ እንደነዚህ ያሉ የተቀናጁ የምልመላ መድረኮች ወሳኝ ናቸው" ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ በላይ አክለውም አዲስ አበባ የሀገሪቱ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማዕከል እንደመሆኗ፣ በስፖርቱም ዘርፍ 'አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን' ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ቀዳሚውን ሚና እንድትጫወት እየተሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ስፖርተኞቹ በቴክኒክ ብቃታቸው ብቻ ሳይሆን በስነ-ምግባር የታነጹ እንዲሆኑ፣ ቢሮው አስፈላጊውን ቁሳቁስና ሙያዊ ድጋፍ በማቅረብ የከተማዋን የስፖርት ስም ከፍ ለማድረግ እንደሚተጋ አቶ በላይ አረጋግጠዋል።

ወ/ሮ ካባ መብራት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው እንደ ሀገር የተጀመረውን አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን የመገንባት ጉዞ ለማሳካት የክፍለ ከተማው አስተዳደር ለታዳጊዎች ስልጠና ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገልጸዋል። ክፍለ ከተማው በምልመላው ሂደት 6 ታዳጊዎችን ለልዩ ስልጠናው ማስመረጥ መቻሉ የተጀመረው ስልጠና ውጤታማ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን፣ ይህ ስኬት በቀጣይም በሳይንሳዊ መንገድ የታገዘ የታዳጊዎች ስልጠና በስፋት እንዲቀጥል እና ለሀገር ኩራት የሚሆኑ ተተኪዎችን ለማፍራት የሚያስችል ጠንካራ መሠረት እንደሚሆን አረጋግጠዋል።

በምልመላ ውድድሩ ከ11 ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ 300 ስፖርተኞች የተሳተፉ ሲሆን አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የውድድሩ ሻምፒዮና በመሆን የዋንጫ በመሆን የወርቅ ሜዳልያና የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን ቦሌ እና ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ የብርና የነሐስ ሜዳልያ ተሸላሚ መሆን ችለዋል።

ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 6 ተጨዋቾችን በማስመረጥ ልዩ የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችሎል።

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.