ጥበብና ዕውቀት ለተሻለ ውጤታማ ስራ በሚል መሪ ሃሳብ የሰኞ የእውቀት ሽግግር መድረክ ተካሄደ ጥር 25 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
ጥበብና ዕውቀት ለተሻለ ውጤታማ ስራ በሚል መሪ ሃሳብ የሰኞ የእውቀት ሽግግር መድረክ ተካሄደ
ጥር 25 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ዘወትር ሰኞ ከስራ ስዓት መግቢያ በፊት የሚያካሂደው የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ጥበብና ዕውቀት ለተሻለ ውጤታማ ስራ በሚል መሪ ሃሳብ ተካሄደ
በመድረኩ ላይ የተገኙት የቢሮው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራ እንዲህ ያሉ የዕውቀት ሽግግር መድረኮች ለተቋሙ ዕድገትና ለሰራተኛው የአስተሳሰብ መበልጸግ ያላቸውን ፋይዳ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች አጠቃቀም ላይ በየደረጃው የሚደረጉ ውይይቶች የሳምንቱ ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫ መሆናቸውን ያመላከቱት አቶ ሚልዮን በስራው ላይ የተመደቡ ኮሚቴዎች ጠንካራ ክትትል እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡
ጥበብንና ዕውቀትን በማነጻጸር ጥልቅ ትንታኔ የሰጡት የማህበረሰብ ስፖርት ማስፋፊያ ዳይሮክቶሬት ዳይሬከተር አቶ እንግዳወርቅ ዳንኤል የጥበብን ምንነትና አምዶች ለማብራራት ወደ ጥንታዊያኑ የግሪክ ፈላስፎች ዘንድ ተጉዘው ካለን የስራ ባህል ጋር አዛምደዋል፡፡
የሶቅራጥስን "ራስን ማወቅ"፣ የፕላቶን "የሃሳብ ልዕልና" እና የአርስቶትልን "ተግባራዊ ጥበብ" እንደ ማሳያ የጠቀሱት አቶ እንግዳወርቅ ጥበብ ከዕውቀት በላይ የሕይወት መመሪያ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ዕውቀትና ጥበብ በማቀናጀት ከሰራን ውጤታማ መሆን እንችላለን ያሉት አቶ እንግዳወርቅ ገንዘብን በአግባቡ መጠቀምና ከስህተት መማር የጥበብ ምልክቶች መሆናቸውን አብራርተዋል።
https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.