ስብዕና ልማት ለትውልድ፦ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ስብዕና ልማት ለትውልድ፦ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የተገነባው ዘመናዊ የስፖርት ማዕከል ተመረቀ!" ጥር 27 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

ስብዕና ልማት ለትውልድ፦ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የተገነባው ዘመናዊ የስፖርት ማዕከል ተመረቀ!"

ጥር 27 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የወጣቶችን የስፖርት ተሳትፎ እና አካላዊ ብቃትን ለማሳደግ ታላቅ ተስፋ ሰጪ የሆነ ዘመናዊ የስብዕና መገንቢያ (ጂምናዚየም) በትላትናው እለት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ ወጣት ክብረዓለም ደምሴ እንደገለጹት፤ እንዲህ ያሉ ማዕከላት ወጣቶችን ለሀገር አቀፍና ለዓለም አቀፍ ውድድሮች ብቁ ለማድረግ ሚናቸው ከፍተኛ ነው ብለዋል

የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ተክሌ ማዕከሉ በዘመናዊ የስፖርት መሣሪያዎችና በብቁ አሰልጣኞች የተደራጀ መሆኑን ጠቁመዋል።

የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ እጩ ዶ/ር አንዱዓለም አሸብር ማዕከሉ ለእግር ኳስ፣ ለአትሌቲክስና ለሌሎች ስፖርቶች መሰረት የሚጥል መሆኑን ገልጸዋል።

የወረዳው ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ቦንቱ ታደሰ እና የማዕከሉ ኃላፊ አቶ ዘበና ታምሩ ወጣቶች ከሱስና ከጤና ችግሮች ርቀው በስፖርት እንዲታነጹ ጥሪ አቅርበዋል።

https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.