በልደታ ክፍለ ከተማ የ"ስብዕና ልማት ለትውልድ" ስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ ግንባታ በይፋ ተጀመረ! ጥር 27 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
በልደታ ክፍለ ከተማ የ"ስብዕና ልማት ለትውልድ" ስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ ግንባታ በይፋ ተጀመረ!
ጥር 27 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
በልደታ ክፍለ ከተማ አገር ተረካቢና በስነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ ለማፍራት ትልቅ ፋይዳ ያለው የ"ስብዕና ልማት ለትውልድ" የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሄደ።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ: "መንግስት ከለውጡ በኋላ አገር ተረካቢ ትውልድ ለማነፅ የሚያስችሉ የስብዕና መገንቢያ ማዕከላትን እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በመስራት ላይ ይገኛል።
አሁን በልደታ ክፍለ ከተማ የሚገነባው ሜዳም ሳቢ፣ ማራኪና ጥራቱን የጠበቀ ሲሆን፤ ለሌሎች አካባቢዎችም እንደ ሞዴል የሚያገለግል መሆኑን አቶ በላይ ገልፀዋል።
ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው "የስፖርት ማዘውተሪያዎችን ማስፋፋት ወጣቶችን ንቁ፣ ጤናማና ግብረ-ገብነትን የተላበሱ ለማድረግ ያስችላል። ንቁና ብቁ ትውልድ የማፍራት ኃላፊነት የሁላችንም ድርሻ በመሆኑ፣ ይህ ፕሮጀክት ለነገ አገር ተረካቢዎች ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።"
አቶ ክብረዓለም ደምሴ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ም/ቢሮ ሀላፊ: "በርካታ የስፖርት ማዘውተሪያዎችን በጥራትና በአጭር ጊዜ ገንብተን እያስመረቅን እንገኛለን። ይህንም ሜዳ በተቀመጠለት ጊዜ ተጠናቆ ለስፖርት ቤተሰቡ ክፍት እንደሚደረግ ተናግረዋል ።"
የፕሮጀክቱ ስራ ተቋራጭ አቶ ፋአድ ይብራሂም በበኩላቸው፣ የተሰጣቸውን እድል በመጠቀም ስፖርቱ የተሰጠውን ትኩረት በሚመጥን መልኩ ስራውን በጥራትና በጊዜው አጠናቀው እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከልደታ ወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት ከታን ኢንጂነሪግ ጋር በመተባበር በወረዳ 08 ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከል የሚለማው ስፖርት ማዘውተርያ ስፋ ግንባተው በ3 ወራት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተመልክቷል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.