የዳንስ ፊትነስ አሰልጣኝ ቶማሴ ሀይሉ በባህሬን...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የዳንስ ፊትነስ አሰልጣኝ ቶማሴ ሀይሉ በባህሬን ያገኘውን እውቅና ለአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አሰረከበ።

የዳንስ ፊትነስ አሰልጣኝ ቶማሴ ሀይሉ በባህሬን ያገኘውን እውቅና ለአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አሰረከበ። ጥር 27 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በዳንስ ፊትነስ ስፖርት ዘርፍ በኢትዮጵያ ስመ ጥር የሆነው አሰልጣኝ ቶማሴ ሀይሉ በቅርቡ በባህሬን በተካሄደውና ከ3,000 በላይ ሰዎች በተሳተፉበት “ሩጫ ከጀግኖች ጋር” (Run with Legends) መርሃ ግብር ላይ ላሳየው ድንቅ ብቃትና ላበረከተው አስተዋጽኦ የተሰጠውን የክብር ሽልማት ለአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን አስረከበ። በዚህ ታላቅ መርሃ ግብር ላይ የኢትዮጵያ የኩራት ምልክቶች የሆኑት ረዳት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና አትሌት ጉዳፍ ፀጋየ በክብር እንግድነት ተጋብዘዋል። አሰልጣኝ ቶማስ ሽልማቱን ባስረከበበት ወቅት እንደገለጸው፤ ለዚህ ስኬት እንዲበቃ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እያደረገለት ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍና ማበረታቻ ትልቅ አቅም እንደሆነው ጠቅሶ ምስጋናውን አቅርቧል። የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ሽልማቱን በተረከቡበት ወቅት እንደገለጹት አሰልጣኝ ቶማስ በውጭ ሀገር የሀገሩን ስምና ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ማድረግ መቻሉ ለቢሮአችን ብቻ ሳይሆን ለሀገራችንም ኩራት ነው ያሉ ሲሆን ይህ ውጤት በዘርፉ ለሚሰማሩ ወጣቶች ትልቅ መነሳሳትን እንደሚፈጥር ተናግረዋል። ቢሮአችን እንደ ቶማስ ያሉ በፈጠራ የታጀቡና ለወጣቱ አርአያ የሚሆኑ ስፖርተኞችን መደገፉን አጠናክሮ አሰንደሚቀጥል አሳውቀዋል። አቶ በላይ አክለውም፣ ስፖርት ከጤናማነት ባለፈ ሀገርን በዓለም መድረክ የማስተዋወቅ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ፋይዳ እንዳለው ገልጸው፣ ወጣቶች በያሉበት የስፖርት ዘርፍ በትጋት እንዲሰሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። አሰልጣኝ ቶማስ በባህሬን በነበረው ቆይታ በዳንስ ፊትነስ ስልጠናው ከ3 ሺህ በላይ ተሳታፊዎችን በማነቃቃት የኢትዮጵያን ስም ማስጠራት መቻሉ ይታወሳል።

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.