የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ባለፉት አምስት ዓመታት 1.6 ሚሊዮን ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መስራቱን አሳወቀ
የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ባለፉት አምስት ዓመታት 1.6 ሚሊዮን ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መስራቱን አሳወቀ
ጥር 28 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ባለፉት አምስት የለውጥ ዓመታት ከሲቪክ ማህበራት ጋር በጋራ ስለተከናወኑ ተግባራትና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት አካሄደ።
በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን፤ ባለፉት አምስት የለውጥ ዓመታት መንግስት የወጣቱን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።
በተለይም ወጣቶች በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካዊ መስኮች ያላቸው ተሳትፎ እንዲጎለብት ከሲቪክ ማህበራት ጋር የተፈጠረው ቅንጅት ለተመዘገቡ ውጤቶች መሰረት መሆኑን አስገንዝበዋል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን እንደገለጹት፤ ባለፉት አምስት የለውጥ ዓመታት የከተማዋን ወጣቶች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሲቪክ ማህበራት ጋር የተቀናጀ ስራ ተከናውኗል ብለዋል።
አቶ በላይ በንግግራቸው ወቅት ትኩረት ሰጥተው ካነሱት ነጥቦች መካከል የወጣቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አንዱ ነው። "ባለፉት አምስት ዓመታት በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ለ1.6 ሚሊዮን ወጣቶች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል" ያሉት ኃላፊው፣ ይህም ወጣቱ ራሱን እንዲችልና ለከተማዋ እድገት የራሱን ድርሻ እንዲያበረክት ትልቅ አቅም መፍጠሩን ገልጸዋል።
በተለይም የወጣቶችን የኢኮኖሚ ጥንካሬ ለመገንባት በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ለ1.6 ሚሊዮን ወጣቶች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ኃላፊው አረጋግጠዋል።
አቶ በላይ ደጀን አክለውም፤ የሲቪክ ማህበራትና የከተማው ወጣቶች በቀጣይ በሚካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደቱን እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ክብረ ዓለም ደምሴ በበኩላቸው፤ በአምስቱ ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የሚተነትን ዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል።
በሪፖርቱም ቢሮው እንደ የአዲስ አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን፣ የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር፣ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማህበር፣ የኢትዮጵያ ደም ለጋሾች ማህበር እና የአረንጓዴው ጎርፍ የአንጋፋ አትሌቶች መረዳጃ ማህበር ካሉ የሲቪክ ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራቱ ለውጤቱ መገኘት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉ ተመልክቷል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ በቀጣይ የመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ ወጣቶች በከተማዋ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ላይ ያላቸውን ድርሻ ለማሳደግ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ተሳታፊ የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች ባለፉት ዓመታት የታዩ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና በወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ እንዲሁም በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ መንግስት የሚያደርገው ድጋፍ እንዲያድግ ጥያቄና አስተያየታቸውን አቅርበዋል።
ቢሮውም ለተነሱት ነጥቦች ምላሽና የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል።
https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.