የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ9ኛው ሀገር አ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ9ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ምዘና ውድድር የሚሳተፈውን ልዑክ በክብር ሸኘ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ9ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ምዘና ውድድር የሚሳተፈውን ልዑክ በክብር ሸኘ

ጥር 30 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አዳማ ከተማ ለሚካሄደው 9ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ምዘና ውድድር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ 630 አባላትን ያካተተውን የልዑካን ቡድን ዛሬ በይፋ ሸኝቷል።

በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ለልዑካን ቡድኑ አባላት የሥራ መመሪያና የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኃላፊው በመልዕክታቸውም፤ ከተማ አስተዳደሩ በውድድሩ ላይ የሚሳተፈው በከፍተኛ ዝግጅትና በላቀ ተነሳሽነት መሆኑን ገልጸው፣ ስፖርተኞቹ የከተማዋን ስም የሚያስጠራ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አሳስበዋል።

አቶ በላይ ባስተላለፉት መመሪያ ላይ ልዩ ትኩረት የሰጡት ሌላው ነጥብ ስፖርታዊ ጨዋነትን የተመለከተ ሲሆን፤ "ውጤት የሚረጋገጠው በሜዳ ላይ ብቃት ብቻ ሳይሆን በላቀ ስነ-ምግባርም ጭምር ነው" ብለዋል።

ታዳጊ ስፖርተኞቹ ከሌሎች ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከሚመጡ አቻዎቻቸው ጋር በሚያደርጉት ፉክክር ፍጹም ስፖርታዊ ጨዋነትን የተላበሰ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ፣ የዳኞችን ውሳኔ እንዲያከብሩ እና የአዲስ አበባን ስልጣኔና ጨዋነት በውድድሩ መድረክ እንዲያንጸባርቁ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በውድድሩ ላይ ተሳታፊ የሆኑ 14ቱም የስፖርት አይነቶች የተቀናጀ ጥረት በማድረግ የአጠቃላይ ሻምፒዮናነትን ክብር እንዲያስጠብቁ አቶ በላይ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

ውድድሩ የውጤት ብቻ ሳይሆን፣ ወደፊት ሀገርን በዓለም አቀፍ መድረክ የሚወክሉ "ኤሊት" ስፖርተኞች የሚመረጡበት መሆኑን ተገንዝበው ታዳጊዎች ያላቸውን ክህሎት እንዲያሳዩ የቢሮ ሀላፊው አበረታተዋል።

በመጨረሻም አቶ በላይ ለመላው ስፖርተኞች፣ አሰልጣኞችና የቡድን መሪዎች መልካም እድል እንዲገጥማቸውና ጉዟቸው የሰላምና የድል እንዲሆን በመመኘት ሽኝቱን አጠናቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማን በመወከል ወደ ስፍራው ያቀናው ይህ የልዑካን ቡድን 630 አባላትን የያዘ ሲሆን፣ ውድድሩ ከየካቲት 01 እስከ የካቲት 08 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአዳማ ከተማ የሚካሄድ ይሆናል።

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.