በአዲስ አበባ ለ350 የቴኳንዶ ስፖርተኞች ዓለም አቀፍ የሙያ ማሻሻያ ስልጠና እየተሰጠ ነው
በአዲስ አበባ ለ350 የቴኳንዶ ስፖርተኞች ዓለም አቀፍ የሙያ ማሻሻያ ስልጠና እየተሰጠ ነው
ጥር 30 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
በአዲስ አበባ ከተማ የኢንተርናሽናል ትራዲሽናል ቴኳንዶ ስፖርትን ይበልጥ ለማስፋፋትና የቴክኒክ አቅምን ለማሳደግ ያለመ የሙያ ማሻሻያ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
ከጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በ4 ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል እየተሰጠ በሚገኘው በዚህ ስልጠና ላይ ከ350 በላይ ሰልጣኞች እየተሳተፉ መሆኑ ታውቋል።
ስልጠናውን በዋናነት እየመሩት የሚገኙት ከአውስትራልያ የመጡት ታዋቂው የዘርፉ ምሁር ግራንድ ማስተር ሚኪኤል ዳሂር እና ረዳት አሰልጣኞቻቸው ናቸው።
የስልጠናው ዋነኛ ግብ የኢንተርናሽናል ትራዲሽናል ቴኳንዶ ስፖርት በከተማዋ ውስጥ በስፋት እንዲሰራጭ ማድረግ ሲሆን፣ በተለይም አሰልጣኞችና ስፖርተኞች ያላቸውን የቴክኒክ ብቃት ከዓለም አቀፍ ደረጃ ጋር ለማጣጣምና ለማዘመን መሆኑ ተገልጿል።
ግራንድ ማስተር ሚኪኤል ዳሂር በቆይታቸው አዳዲስ የውድድር ስልቶችን፣ የዳኝነት መርሆዎችንና የቴኳንዶ ስፖርት ፍልስፍናን በተግባር ለሰልጣኞቹ እያጋሩ ይገኛሉ።
ስልጠናው እስከ ነገ የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፣ በማጠቃለያውም ለሰልጣኞች የእውቅና ምስክር ወረቀት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
86Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 84 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.