የአዲስ አበባ ስፖርት ልዑካን በ9ኛው ሀገር አቀ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የአዲስ አበባ ስፖርት ልዑካን በ9ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊዎች ውድድር መክፈቻ ላይ የከተማዋን ገፅታ በአምባሳደርነት በደመቀ ሁኔታ አስተዋወቀ

የአዲስ አበባ ስፖርት ልዑካን በ9ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊዎች ውድድር መክፈቻ ላይ የከተማዋን ገፅታ በአምባሳደርነት በደመቀ ሁኔታ አስተዋወቀ

የካቲት 01 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

በአዳማ ከተማ በድምቀት በተከፈተው 9ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር ላይ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ልዑካን ቡድን የከተማዋን ባህል፣ ስፖርታዊ ጨዋነት እና እድገት የሚያንፀባርቅ አቀራረብ በማሳየት የአምባሳደርነት ሚናውን በብቃት ተወጥቷል።

ልዑኩ በመክፈቻው ስነ-ስርዓት ላይ ባሳየው ወጥ የሆነ የአለባበስ ስርዓት፣ ስልጡን ሰልፍ እና ስፖርታዊ ጨዋነት አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ መዲና መሆኗን በሚመጥን መልኩ ከተማዋን ለተቀረው የሀገሪቱ ልዑካን እና ለታዳሚው አስተዋውቋል።

ይህ እንቅስቃሴ የከተማዋን መልካም ገፅታ ከመገንባት ባለፈ፣ በታዳጊ ስፖርተኞች መካከል ያለውን ወንድማማችነት እና አንድነትን በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ አምባሳደራዊ ፋይዳ ነበረው።

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ወክለው ወደ ስፍራው ያመሩት 630 የልዑካን ቡድን አባላት በውድድሩ በሚካሄዱ 14 የስፖርት አይነቶች ላይ የሚሳተፉ ሲሆን፣ በመክፈቻው ላይ የታየው የቡድን መንፈስ በውድድሩም ላይ እንደሚደገም ይጠበቃል።

ታዳጊ ወጣቶች በስፖርታዊ ስልጠና የደረሱበትን የክህሎት ደረጃ ለመመዘን የሚካሄደው ይህ መድረክ፣ አዲስ አበባ ለተተኪ ስፖርተኞች የምትሰጠውን ትኩረትና በዘርፉ ያላትን የበላይነት ለማሳየት ምቹ አጋጣሚ ፈጥሯል።

 

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.