9ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስል...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

9ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና የምዘና ውድድር በደማቅ የመክፈቻ ዝግጅት ተጀመረ

9ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና የምዘና ውድድር በደማቅ የመክፈቻ ዝግጅት ተጀመረ

የካቲት 01 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የታዳጊ ስፖርተኞች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 9ኛው የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር በአዳማ ሳይስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ በድምቀት ተጀመረ።

ውድድሩን ያስጀመሩት የኢፌድሪ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሸዊት ሻንካ መንግስት ለስፓርት ዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት ከ17 ሺህ በላይ ሜዳዎችን ገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉን ገልጸዋል።

በታዳጊ ስፓርተኞች ላይ መስራት ለነገ ስፖርት መሰራት መጣል ነው ያሉት ሚንስትሯ ሀገርን ሊያስጠሩ የሚችሉ ስፖርተኞችን ለማፍራት የተቀናጀ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በታዳጊዎች ላይ መስራት የነገውን የኢትዮጵያ ስፖርት መሰረት መጣል ነው ያሉት ሚንስትሯ ስፖርት የዜጎችን አካላዊ ከመጠበቅ ባሻገር ለዲፕሎማሲያዊ ስኬት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል

ስፖርት ለወንድማማችነት እና ሕብረ ብሔራዊ ጠንካራ አገር ለመገንባት ወሳኝ ነው ያሉት የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ ጀልዱ ተተኪ ስፓርተኞችን የማፍራት ስራ ላይ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል

ስፖርትን ከቱሪዝም ጋር በማገናኘት የምሽት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የሚያሴልጡ ፋሲሊቲዎች መሟላታቸውን የገለጹት ከንቲባው

በከተማዋ እየተካሄደ ያለው የኮሪደር ልማት ለስፖርት መሰረተ-ልማት ግንባታ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አብራርተዋል።

ወላይታ ሶዶ በተካሄደው ስምንተኛው የታዳጊ ወጣቶች መድረክ ላይ ስኬታማ አትሌቶች መገኘታቸውን ያወሱት የዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ካንትሪ ኃላፊ ዶክተር አቡበከር ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ እና በአህጉር አቀፍ ውድድር ውጤታማ ለማድረግ አመጋገብን መሰረት ያደረገ ልምምድ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል

+3

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

130You፤ Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 127 ሌሎች

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.