በአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ዘወትር ሰኞ የሚካሄደው የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መድረክ ዛሬም በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል ።
በአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ዘወትር ሰኞ የሚካሄደው የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መድረክ ዛሬም በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል ።
የካቲት 02 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
በአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ዘወትር ሰኞ የሚካሄደው የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መድረክ ዛሬም በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል።
የዕለቱ የእወቀት ሽግግር "የተቋም ባህል ግንባታ (Organizational Culture Building)" በሚል ርዕሰ ጉዳይ አቶ ገደፋው ውበቴ የቢሮው የወጣቶች ግንዛቤና ተሳትፎ ከፍተኛ ባለሙያ አቅርበዋል።
በሰነዱ ላይ እንደተመለከተው፣ አንድ ተቋም ስኬታማ ሊሆን የሚችለው በውስጡ የሚሰሩ ሰራተኞችን እውቀት፣ አስተሳሰብና አመለካከት በተቀናጀ መልኩ መገንባትና ተቋማዊ ማድረግ ሲቻል ነው።
ጠንካራ ተቋማዊ ባህል መገንባት ማለትም፦ የተቋሙን ውጤታማነት ማሳደግ፤
የደንበኞችንና የሰራተኞችን እርካታ ማሻሻል፤
በተቋሙ ውስጥና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ማጎልበት እንደሆነ ተመላክቷል።
በተለይም የሰዓት አጠቃቀምን፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን እና ሌሎች የቢሮውን ውጤታማነት የሚያረጋግጡ ተግባራትን እንደ ባህል መውሰድና መተግበር ለተቋሙ ገጽታ ግንባታና ለቀጣይነቱ ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ተገልጿል።
በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉተሰ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሚሊዮን ኮራን ተቋማዊ ባህል ማለት ዝም ብሎ የሚገነባ ሳይሆን እያንዳንዳችን በየቀኑ የምናሳየው የስራ ተነሳሽነትና ለተገልጋዩ የምንሰጠው ክብር ድምር ውጤት ነው።
እውቀትን ወደ ተግባር በመለወጥ፣ ሰዓትን በአግባቡ በመጠቀምና በቅንጅት በመስራት ቢሯችንን ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉ አቶ ሚሊዮን አሳስበዋል።
ይህ የእውቀት ሽግግር መድረክ የሰራተኞችን አቅም ከመገንባት ባለፈ፣ የተቀላጠፈና ዘመናዊ አሰራርን በቢሮው ውስጥ ለማስፈን ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተመላክቷል
https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.