የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖ...

image description
- ውስጥ supporter    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ምዘና ሊጀምር ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ምዘና ሊጀምር ነው

የካቲት 02 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማን ለማካሄድ የምዘና ቡድኖችን ወደ ሥራ አሰማራ።

ቢሮው የምዘና ሂደቱን በይፋ ከመጀመሩ በፊት ምዘናውን ለሚያካሂዱ አካላት ገለፃ (ኦሬንቴሽን) ሰጥቷል።

ይህ የግማሽ ዓመት የዘርፍ ተቋማት ምዘና በቢሮው ሥር የሚገኙ የክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤቶች፣ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት፣ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከላት እና የቢሮው ዳይሬክቶሬቶች የሚያካትት ይሆናል።

በገለፃ መድረኩ ላይ የተገኙ የቢሮው የስራ ሀላፊዎች እንደገለጹት፤ ምዘናው የሥራችን መስተዋት ነው፤ ባለፉት ስድስት ወራት የወጣቶቻችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የስፖርት ዘርፉን ለማሳደግ የሄድንበትን ርቀት በተጨባጭ መረጃ የምንመዝንበት ይሆናል ብለዋል።

አክለውም የምዘና ሂደቱ በግልፅነትና በተጠያቂነት መርህ እንደሚከናወን ገልጸዋል።

የምዘናው ሂደት ትኩረት የሚያደርግባቸው ነጥቦችም በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ የታቀዱ ዕቅዶች ምን ያህል ውጤት እንዳመጡ ለመፈተሽ ነው። በተለይም የከተማዋን ወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንፃር የተከናወኑ ተግባራት በጥልቀት የሚታዩ ይሆናል።

በተጨማሪም የከተማዋን የስፖርት እንቅስቃሴ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን አጠቃቀም እና የስልጠና ማዕከላትን ውጤታማነት መመዘን የሂደቱ ዋነኛ አካል መሆኑ ተገልጿል።

ይህ የምዘና መድረክ ተቋማቱ በስድስት ወራቱ ውስጥ የነበራቸውን ጥንካሬና ድክመት ለይተው እንዲያውቁና በቀሪው ስድስት ወራት ለተሻለ ውጤት እንዲረባረቡ መነሻ እንደሚሆን ይጠበቃል።

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.