በውድድር ወቅት ሰውነት ጫና ውስጥ እንዳይወድቅ አመጋገባችን በማስተካከል ውጤታማ እንሁን!
በውድድር ወቅት ሰውነት ጫና ውስጥ እንዳይወድቅ አመጋገባችን በማስተካከል ውጤታማ እንሁን!
ዛሬ ውድድር ላለባችሁ የአሸናፊነት ቀን እንዲሆን ተመኘን
የካቲት 3 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣታቶችና ስፖርት ቢሮ
የውጤታማ ስፖርተኛ አመጋገብ መመሪያ
ቅድመ-ውድድር
ከውድድር በፊት የሚበላ ምግብ ዋና ዓላማው በጡንቻ ውስጥ በቂ ሃይል ማከማቸት ነው።
ከውድድር 2-3 ሰዓት በፊት፦ በቀላሉ የሚፈጩ ካርቦሃይድሬቶችን (እንደ ፓስታ፣ ሩዝ፣ ወይም ዳቦ) ከቀላል ፕሮቲን ጋር መውሰድ።
ቀንስ፦ ቅባት የበዛባቸው ምግቦች እና ፋይበር (እንደ ሰላጣ) አትብዛ፤ ምክንያቱም በውድድር መሃል ሆድ ላይ ቁርጠት ሊፈጥሩ ይችላሉ።
በውድድር መሃል
ውድድሩ ከ1 ሰዓት በላይ የሚቆይ ከሆነ ጉልበት እንዳያንስህ፡-ሙዝ፣ የደረቁ ፍራፍሬዎች ወይም የስፖርት መጠጦች (Electrolytes) መውሰድ ድካምን ለመከላከል ይረዳሉ።
ድህረ-ውድድር ምገባ፡- ውድድር ሲያልቅ ጡንቻዎች ይደክማሉ፣ ጥቃቅን ስብራትም ሊኖራቸው ይችላል። ውድድር እንዳለቀ በመጀመሪያዎቹ 30 ደቂቃዎች ውስጥ ፕሮቲን እና ካርቦሃይድሬት የተቀላቀለበት ምግብ ወይም መጠጥ (ለምሳሌ፦ ወተት፣ እንቁላል፣ ወይም እርጎ) መውሰድ ጡንቻ ቶሎ እንዲያገግም ያደርጋል፡፡
አስተውሉ፡- በየ15-20 ደቂቃው ውሃ መጠጣት ሰውነት እንዳይደክም እንዳይደርቅ ያግዛል
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
83Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 81 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.




አስተያየቶችዎን ይተዉት.