የዐድዋን ድል በመዘከር የሚካሄደው የ"ዐድዋ ካፕ" ስፖርታዊ ፌስቲቫል በድምቀት ተጀመረ
የዐድዋን ድል በመዘከር የሚካሄደው የ"ዐድዋ ካፕ" ስፖርታዊ ፌስቲቫል በድምቀት ተጀመረ
የካቲት 03 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የ130ኛውን የዐድዋ ድል በዓል ለመዘከር በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው ስፖርታዊ ፌስቲቫልና ውድድር በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።
"ዐድዋ ካፕ" በሚል መሪ ቃል በተጀመረው በዚህ ውድድር ላይ ዘጠኝ የሠራዊት ክፍሎች በአምስት የስፖርት ዓይነቶች ለድል እንደሚፋለሙ ታውቋል።
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን የዐድዋን ድል ለመዘከርና በሠራዊቱ ውስጥ ያለውን አንድነት ይበልጥ ለማጠናከር ያዘጋጀው ይህ ስፖርታዊ ፌስቲቫል ለ3ኛ ጊዜ የተዘጋጀ ነው።
በውድድሩ መክፈቻ ላይ የተገኙት የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ወ/ሮ ማርታ ሉዊጂ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዐድዋ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ሕዝቦች የነፃነት፣ የአሸናፊነትና የአይበገሬነት ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
ሚኒስትር ዲኤታዋ አክለውም፣ የአሁኑ ትውልድ ከታሪካዊው የዐድዋ ድል ትምህርት በመውሰድ በሀገር ግንባታ፣ በልማትና በሰላም ማስከበር ረገድ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ በበኩላቸው፤ የመከላከያ ተቋማት ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ የስፖርት ዕድገት እያበረከቱ ያለውን ሚና አድንቀዋል።
አቶ ዳዊት እንዳሉት፣ የዐድዋን መንፈስ መሠረት በማድረግ በአገር ደረጃ የተጀመረውን የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የአሸናፊነት ጉዞ ማስቀጠል ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ተግባር ነው ብለዋል።
ይህ ስፖርታዊ ፌስቲቫል በሠራዊቱ መካከል ያለውን ወንድማማችነት ከማጠናከር ባለፈ፣ ለሀገራዊ ስፖርት ዕድገት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም ተመላክቷል።
https://linktr.ee/YouthandSport1
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
128Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 126 ሌሎች
1
4
ይውደዱ
አስተያየት
ያጋሩ
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.