ስልጡን ወጣት ለከተማ ሰላምና ለሁለንተናዊ ብልጽ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ስልጡን ወጣት ለከተማ ሰላምና ለሁለንተናዊ ብልጽግና! የካቲት 03 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

ስልጡን ወጣት ለከተማ ሰላምና ለሁለንተናዊ ብልጽግና!

የካቲት 03 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር በመተባበር ሲያካሂደው የቆየው የወጣቶች የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል።

በውይይቱ የሰላም እሴት ግንባታ ላይ የወጣቱ ድርሻ ቀዳሚ መሆኑ ተገልጿል። በተለይም በቅርቡ ለሚካሄደው 7ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ሰላማዊና ፍትሀዊ እንዲሆን ወጣቱ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለጹት፤ ወጣቱ በውይይትና በሃሳብ የበላይነት የሚያምን፣ ነጠላ ትርክቶችን ወደ ጎን በመተው በልማትና በመልካም አስተዳደር ግንባር ቀደም መሆን አለበት ብለዋል።

ወጣቱ ከሀሰተኛ መረጃዎች በመራቅ፣ የሀገርን አንድነት ከሚበታተኑ ሴራዎች ራሱን በመጠበቅና የአካባቢውን ሰላም በንቃት በመጠበቅ የከተማዋን ሰላም ማጽናት እንደሚገባ ወ/ሮ ሊዲያ አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ክብረአለም ደምሴ በበኩላቸው የውጭ ጠላቶችን ሴራ ለመመከትና የጀመርነውን የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠል "የውስጥ ሰላማችን ወሳኝ ነው" ብለዋል።

ወጣቱ ትውልድ ለጠላት የማይተኛ፣ የሃሳብ ጥቃትን የሚመክትና ለከተማው ሰላም ዘብ የሚቆም እንዲሆን በመድረኩ ተመላክቷል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ወጣቶችም በሰጡት አስተያየት፤ መድረኩ ለከተማቸው ሰላም ያላቸውን ኃላፊነት እንዲረዱ እንዳደረጋቸው ገልጸው፣ በተለይም ከመከፋፈልና ከጥላቻ ትርክቶች በመራቅ ለጋራ እድገት መስራት እንደሚገባ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

ወጣቶቹ አክለውም፣ በአካባቢያቸው የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በንቃት በመከላከልና በሰላም አደረጃጀቶች ውስጥ በንቃት በመሳተፍ የከተማዋን ጸጥታ ለማስከበርና መጪው ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አርበኝነት ለመወጣት ቃል ገብተዋል።

#AddisAbaba #PeaceBuilding #EthiopianYouth #PeaceAndSecurity #Prosperity

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.