የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የልምድ ልውውጥ አደረገ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የልምድ ልውውጥ አደረገ
የካቲት 04 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች ልምድ አካፈለ።
በልምድ ልውውጥ መድረኩ ላይ ቢሮው የወጣቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳታፊነት ለማረጋገጥ የዘረጋቸውን ስትራቴጂዎችና ያስመዘገባቸውን ውጤቶችን የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ክብረአለም ደምሴ በዝርዝር አቅርቧል።
በተለይም የወጣቶችን ስብዕና ከመገንባት አኳያ በከተማዋ በሚገኙ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች በዋናነት ተዳስሰዋል።
ቢሮው በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት በኩል ወጣቶች በስነ-ምግባር የታነጹ፣ በፈቃደኝነት አገልግሎት ላይ ንቁ ተሳታፊ የሆኑና ሀገራዊ ራዕይ ያላቸው እንዲሆኑ እያደረገ ያለው ጥረት ለልዑካን ቡድኑ ቀርቧል።
ወጣቶች በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲችሉ ከማድረግ አንጻር የስራ እድል ፈጠራንና ክህሎትን መሰረት ያደረጉ ስራዎች፣ እንዲሁም በፖለቲካዊና ማህበራዊ ውሳኔ ሰጭነት ላይ ያላቸው ተሳትፎ እንዲያድግ የተሰሩ ስራዎች ተብራርተዋል።
በመድረኩ ላይ እንደተገለጸው፣ እንዲህ ያሉ የልምድ ልውውጦች በክልሎች መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት ከማጠናከራቸው ባለፈ፣ ውጤታማ የሆኑ አሰራሮችን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማስፋት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተመላክቷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የስራ ሃላፊዎች በበኩላቸው፣ በአዲስ አበባ ከተማ በወጣቶች ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችና የተደራጁ የስራ መመሪያዎች ለክልላቸው የወጣቶች ስራ መነቃቃትን እንደሚፈጥሩ ገልጸው፤ የተገኘውን ልምድ ከክልላቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ወደ ተግባር እንደሚቀይሩት አረጋግጠዋል።
ሁለቱም ተቋማት በቀጣይም በጋራ ለመስራትና መረጃዎችን ለመለዋወጥ ያላቸውን ዝግጁነት ገልፀዋል።
https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.