በ9ኛው የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር የጅምናስቲክ ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍጹም የበላይነት ተጠናቀቀ
በ9ኛው የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር የጅምናስቲክ ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍጹም የበላይነት ተጠናቀቀ
የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣታቶችና ስፖርት ቢሮ
በ9ኛው የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና የምዘና ውድድር የጅምናስቲክ ውድድር ዛሬ የተጠናቀቀ ሲሆን የአዲስ አበባ አስተዳደር የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ መሆን ችሏል
ተተኪ ስፖርተኞች ድንቅ ብቃታቸውን ባሳዩበት ውድድር የአዲስ አበባ ስፖርት ልዑክ ስድስት የወርቅ 4 የብር እና 5 የነሐስ ሜዴልያ በመሰብሰብ ሻምፒዮና መሆኑን አረጋግጠዋል
አማራ ወርቅ 3 ብር 2 ነሀስ 2 የሁለተኛ ደረጃ ሲይዝ ደቡብ ምዕራብ 3ኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በውድድሩ በሜዳልያ ሰንጠረዡ አናት ላይ በመቀመጥ አጠቃላይ አሸናፊነቱን ባረጋገጠበት መደረክ የፌዴሬሽኑ ፕሬዘዳንት አቶ አጥናፉ ደሴ ተገኝተዋል
የተገኘውን ደማቅ ድል ተከትሎ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ለአሸናፊው ልዑክ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዘዳንቱ በንግግራቸው ፌዴሬሽኑ የጅምናስቲክ ስፖርት እንዲስፋፋ እና ተተኪ ስፖርተኞች የሚፈሩባቸው ስልጠናዎች እንዲጠናከሩ እያደረገ ያለውን ድጋፉ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል
ከፍተኛ ፉክክር በታየበት እና የአዲስ አበባ ልዑካን አሸናፊነታቸውን ባረጋገጡበት በሴት የቡድን ፍጻሜ በወንድ የቡድን እና የግል ውድድር አሸናፊ በመሆን በአንደኝነት ማጠናቀቁን አረጋግጧል
የታዳጊ ስፖርተኞች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል የተጀመረው 9ኛ ዙር የታዳጊዎች ምዘና ውድድር ነገ በማጣሪያ እና በፍጻሜ ውድድሮች እንደሚቀጥል ተመልክቷል
https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.