በስፖርታዊ ጨዋነት የታጀበው የ9ኛው ታዳጊዎች ም...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

በስፖርታዊ ጨዋነት የታጀበው የ9ኛው ታዳጊዎች ምዘና ውድድር ተስፋ ሰጪ ውጤቶች አየተመዘገ እንደሚገኝ ተገለጸ

በስፖርታዊ ጨዋነት የታጀበው የ9ኛው ታዳጊዎች ምዘና ውድድር ተስፋ ሰጪ ውጤቶች አየተመዘገ እንደሚገኝ ተገለጸ

የካቲት 5 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

9ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና የምዘና ውድድር በሜዳ ላይ ከሚታዩ ድሎች በላይ፣ ስፖርታዊ ጨዋነት ጎልቶ የታየበት መሆኑን የሰፓርት ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ አለማየሁ ገለጹ

ከተማ አስተዳደሩ የኢትዮጵያ ስፖርት በሳይንሳዊ ስልጠና በእውነተኛ ዕድሜ እና በላቀ ስነ-ምግባር የታጀበ አዲስ ጉዞ የጀመረበት የውድድር ምዕራፍ መሆኑን አቶ ጎሳዬ ገልጸዋል

ፍጻሜያቸውን ባገኙ ጅምናስቲክ እና የእጅ ኳስ ድሎች የአጋጣሚ ውጤት አይደለም ያሉት አቶ ጎሳዬ በከተማ አስተዳደሩ ለታዳጊ በሰጠው ትኩረት እና በአሰልጣኞች የተቀናጀ ጥረት የተገኘ ፍሬ መሆኑን ገልጸዋል

ስፖርታዊ ጨዋነትን እንደ መመሪያ፣ የዕድሜ ትክክለኛነትን ደግሞ እንደ መርህ መያዝ አስፈላጊ ነው ያሉት አቶ ጎሳዬ የተገኘው ድል ለቀጣዮቹ የቦክስ፣ የውሃ ዋና እና የቅርጫት ኳስ ተወዳዳሪዎች ትልቅ ማበረታቻ ይሆናል ብልዋል

የታዳጊዎች የእግር ኳስ ግስጋሴ በአስገራሚ ሁኔታ መቀጠሉ ለስፖርት ቤተሰቡ ትልቅ ተስፋ የታየበት መሆኑን አቶ ጎሳዬ ገልጸዋል

በደረጃ ቀዳሚ ለመሆን ጠንክሮ መስራት እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ ጎሳዬ በሁሉም የስፓርት ዘርፍ ውጤታማ እንደሚቻል አቅም እንዳለን ለክልሎች የምናሳይበትን አጋጣሚ መጠቀም ይገባል ብለዋል

https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.