አዲስ አበባ ስፖርት ልዑክ በታዳጊዋች ምዘና ውድድር እያሳየ ያለው የበላይነት ቀጥሏል።
አዲስ አበባ ስፖርት ልዑክ በታዳጊዋች ምዘና ውድድር እያሳየ ያለው የበላይነት ቀጥሏል።
የካቲት 5 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
በ9ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና የምዘና ውድድር አንዱ አካል የሆነው የእጅ ኳስ ውድድር በአዲስ አበባ አስተዳደር አሸናፊነት ተጠናቋል
ታዳጊዎቹ በሜዳ ላይ ባሳዩት የተቆራኘ የጨዋታ ስልት፣ ከፍተኛ ጥንካሬ እና ስልታዊ ብቃት ተጋጣሚዎቻቸውን በመርታት የሻምፒዮናነቱን ክብር ተቀዳጅተዋል።
የአዲስ አበባ ቡድን ለድል የበቃው በውጤት ብቻ ሳይሆን፣ ስፖርታዊ ጨዋነትን እና የዕድሜ ተገቢነትን በአርአያነት በመተግበሩ ጭምር በመሆኑ በስፓርቱ አፍቃሪያን አድናቆትን ተችሮታል
የስፓርት ልዑኩ የያዘውን መሪነት አስጠብቆ ለመቀጠል በትኩረት መስራት እንደሚገባ በሽልማት መርሃ ግብሩ ተገልጽዋል።
በእጅ ኳስ ውድድር አዲስ አበባን ተከትለው ቤንሻልጉል ጉምዝ እና ሲዳማ ክልል የብር እና የነሐስ ሜዳልያ ባለቤት ሆነዋል
https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.