አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመስማት የተሳናቸ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመስማት የተሳናቸው የጠረጴዛ ቴኒስ አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ ።

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመስማት የተሳናቸው የጠረጴዛ ቴኒስ አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ ።

የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፓርት ቢሮ

በአዳማ እየተካሄደ ባለው 9ኛው ዙር የታዳጊዎች ምዘና ውድድር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመስማት የተሳናቸው የጠረጴዛ ቴኒስ ውድድር ስድስት የወርቅ ሜዳልያዎችን በማስመዝገብ አጠቃላይ አሸናፊ መሆን ችሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለውድድር ከቀረበው ስድስቱንም የወርቅ ሜዳሊያዎች በመሰብሰብ ነው አጠቃላይ አሸናፊ መሆን የቻለው።

የተመዘገበው ውጤት በስፓርት አካቶ ትግበራ እና ለውድድሩ የተደረገውን ጥልቅ ዝግጅት የሚያሳይ መሆኑ ተመልክቷል

የአዲስ አበባ መስማት የተሳናቸው የቴኒስ ስፖርት ቡድን መሪዎችና አሰልጣኞች ድሉን አስመልክተው እንደገለጹት፣ ስድስቱንም ወርቆች መውሰድ መቻሉ ለከተማዋ አጠቃላይ ውጤት ትልቅ ትርጉም እንዳለው ገልጸዋል

"የታዳጊዎች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ውድድር አዲስ አበባ በሜዳሊያ ሰንጠረዡ አናት ላይ እንደምትገኝ ተመልክቷል።

https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.